ኮሚሽኑ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን እያስመረጠ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከሚገኙ 9 ወረዳዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን የሚያስመርጥበትን መርሐ-ግብር አስጀምሯል፡፡ በሐረር ከተማ ጨለንቆ የባህል አዳራሽ በመከናወን ላይ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ከ800 በላይ የማህበረሰብ ተወካዮችን እያሳተፈ ይገኛል፡፡ በዚህ መርሐ-ግብር ከበዴሳ ከተማ አስተዳደር፣ ከዳሩ ለቡ፣ ከሜኤሶ፣ ከጭሮ፣ ከዶባ፣ ከሸነን ዲጎ፣ ከኦዳ ቡልቱ ፣ከቦኬ እና ከአንጫር ወረዳዎች የመጡ […]