የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 108 የዩንቨርስቲ መምህራንን አሰለጠነ፡፡

ኮሚሽኑ ከመጋቢት 16 እስከ 17/2016 ዓ.ም በአጀንዳ ማሰባሰቡ ሂደት ላይ እገዛ የሚያደርጉ ከተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመጡ108 አወያይ መምህራንን አሰልጥኗል፡፡ ስልጠናውን የወሰዱ መምህራን በቀጣይ ኮሚሽኑ ለሚያካሂደው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት በማወያየት የበኩላቸውን አስተዎጽኦ የሚያበረክቱ ናቸው ተብሏል:: ኮሚሽኑ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚያከናውነው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ግልፅኝነት፣ አሳታፊነት እና ተዓማኒነት እንዲኖረው ስልጠናውን የወሰዱ መምህራን ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ተገልጧል፡፡