ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሲያካሂድ የቆየውን የተወካዮች መረጣ አጠናቀቀ፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ ሲያስመርጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ የክልሉ የተወካዮች መረጣ 12 ዞኖችን በማካተት ሲከናወን የቆየ ሲሆን 9,300 የሚሆኑ ተሳተፊዎችን የሂደቱ አካል አድርጓል፡፡ በዚሁ ክንውን ተሳታፊዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚወክሏቸውን ተወካዮቻቸውን ከመምረጣቸው ባሻገር በሀገራዊ ምክክሩ ዙሪያ ግንዛቤ […]
ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ በማስመረጥ ላይ ይገኛል፡፡
በኬሌ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር በዞኑ ከሚገኙ 2 ወረዳዎች እና 1 የከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 300 የሚሆኑ ተሳታፊዎችን በማሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ሁለት ተወካዮች ከአንድ ተጠባባቂ ጋር እንዲመርጡ ይደረጋል፡: