ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ አስመረጠ፡፡
በቱርሚ ከተማ የተካሄደው ይህ መርሐ-ግብር ከስድስት ወረዳዎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 700 የሚሆኑ ተሳታፊዎችን በማሳተፍ ተከናውኗል፡፡ በሂደቱ ለተሳታፊዎቹ በሀገራዊ ምክክሩ ዙሪያ እንዲሁም በሂደቱ በተወካይ ተሳትፎ በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡርጂ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እያስመረጠ ይገኛል፡፡
በሶያማ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ከአንድ ወረዳ እና አንድ የከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 200 የሚሆኑ ተሳታፊዎችን በማሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡ በሂደቱ ኮሚሽኑ ለተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች በባለሙያ ገላፃ የተደረገላቸው ሲሆን ከዚህ በመቀጠልም ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ተወካዮች እንዲመርጡ ይደረጋል፡፡