የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ እና ጎፋ ዞኖች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ አስመረጠ፡፡

south et gamo

በአርባ ምንጭ እና ሳውላ ከተሞች በትይዩ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የጋሞ እና ጎፋ ዞኖች የተወካዮች መረጣ ከየወረዳው የተወከሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮችን በማካተት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የጋሞ ዞን የተወካዮች መረጣ ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን 1,800 የሚሆኑ ተሳታፊዎች 20 ወረዳዎችንና የከተማ አስተዳደሮችን በመወከል ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ መርሐ-ግብሩም የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል […]

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ በማስመረጥ ላይ ይገኛል፡፡

sheger city

በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ 1,300 የሚሆኑ የሁሉም ክፍለ ከተሞች ተሳታፊዎችን እያሳተፈ ይገኛል፡፡ በሂደቱም ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ በመቀጠልም ውይይቶች ይደረጉና ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ […]