ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን እያስመረጠ ነው፡፡
ከየካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሺኒሌ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በአጠቃላይ 1100 የሚሆኑ ተሳታፊዎችን ያሳትፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በመድረኩ ከአይሻ፣ ሀዳጋላ እና ሺኒሌ ወረዳዎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ለመምረጥ ተገኝተዋል፡፡ መርሐ-ግብሩ በተመሳሳይ ሁኔታ በቀጣዮቹም ሁለት ቀናት የተቀሩትን የዞኑን ወረዳዎች በማሳተፍ ይቀጥላል፡፡ ለመድረኩ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር […]
ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እያስመረጠ ነው፡፡
የዞኑ የተወካዮች መረጣ በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ እየተከናወነ ሲሆን ከ10 ወረዳዎች የተውጣጡ 1,200 የሚሆኑ የተለያዩ ማህበረሰብ ተወካዮች ተሳታፊ እየሆኑበት ይገኛል፡፡ በመድረኩ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል […]