ኮሚሽኑ ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች ጋር ውይይት አደረገ፡፡

በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው በዚሁ መድረክ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደቶች ላይ ንቁ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ግንዛቤን ለመፍጠር ታስቦ በተዘጋጀው መድረክ ከ 250 በላይ የተቋማት ተወካዮች ታድመውበታል፡፡ በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ኮሚሽኑንና የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን በተመለከተ የተለያዩ ገለፃዎችና ማብራሪያዎች ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መሰረት ስለ ሀገራዊ ምክክር መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ፣ ሀገራዊ ምክክር ለሀገራችን ኢትዮጵያ ስላለው ፋይዳ፣ […]