ኮሚሽኑ የሲዳማ ክልል የተሳታፊዎች ልየታን አድርጓል
ሰኔ 01 ቀን 2015 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የተጀመረው የሲዳማ ክልል የተሳታፊዎች ልየታ በይርጋለም፣አለታ ወንዶ እና በንሳ ከተሞች ቀጥሎ ሰኔ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ በክልሉ ከሚገኙ 45 ወረዳዎች ከተውጣጡና በእያንዳንዳቸው ከሚኖሩ ዘጠኝ የማህበረሰብ ክፍሎች ሀምሳ ሀምሳ ተሳታፊዎች የሂደቱ አካል እንዲሆኑ በማድረግ (በአንድ ወረዳ 450) በአጠቃላይ ከ20,000 በላይ ተሳታፊዎች የሂደቱ ተካፋይ ሆነዋል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች በተከናወኑ […]
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶስት ክልሎችና በአንድ የከተማ መስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ተባባሪ አካላት ስልጠናን ሰጥቷል፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶስት ክልሎችና በአንድ የከተማ መስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ተባባሪ አካላት ስልጠናን ሰጥቷል፡፡ በተሳታፊ ልየታ አተገባበር ላይ የተሰጠው ይህ ስልጠና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ፣ በሲዳማ እና በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር ለሚገኙ ከየወረዳው ለተውጣጡ የኮሚሽኑ ተባባሪ አካላት ነው፡፡ ስልጠናው በቦንጋ፣ሐዋሳ እና ድሬዳዋ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን የሁለት ቀናት ጊዜን ወስዶ ግንቦት 23 […]
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 35 አባላትን ያቀፈ የአማካሪ ኮሚቴን ማቋቋሙን ይፋ አድርጓል
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 35 አባላትን ያቀፈ የአማካሪ ኮሚቴን ማቋቋሙን ይፋ አድርጓል፡፡ ኮሚሽኑ ይህንን የገለፀው ዛሬ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም ከኮሚቴው አባላት ጋር ለመተዋወቅ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ሲሆን ከአባላቱም ጋር ገንቢ ውይይትን አድርጓል፡፡ ኮሚሽኑ በኮሚቴው እንዲካተቱ የጋበዛቸው ግለሰቦች በተለያየ መልኩ ለኮሚሽኑ ስራዎች ድጋፎችን የሚያደርጉ ሲሆን በተለያየ ልምድ እና ሙያ ውስጥ እንዳሉም ተገልጿል፡፡ ለዚህም ማሳያ […]
ኮሚሽኑ በአዳማ ከተማ የውይይት መድረኮችን አካሂዷል
ታህሳስ 22-23 ቀናት 2015 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሲቪክ ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም የዞኖችና ወረዳዎች ኃላፊዎች ጋር በአዳማ ከተማ የውይይት መድረኮችን አካሂዷል፡፡ በሁለቱ ቀናት የውይይት መድረኮች ተሳታፊዎች ኮሚሽኑ ባዛጋጃቸው የአሰራር ስርዓቶች ላይ አስተያቶችን የሰጡ ሲሆን በቡድን ውይይቶችን በማካሄድ በርካታ ግብዓቶችን ሰጥተዋል፡፡