ሰብዓዊ መብትን የሚመለከቱ የመወያያ አጀንዳዎች ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ቀረቡ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት፣ የሰብዓዊ መብትና የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በሚመለከት ለመወያያ ይሆናሉ ያላቸውን አጀንዳዎች፣ ለኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አቀረበ፡፡ ኅብረቱ ማክሰኞ ታኅሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው የምክክር መድረክ፣ አጀንዳዎቹን ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተወካዮች ሲያቀርብ የኅብረቱ ኃላፊዎች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ለአገራዊ ምክክሩ የሚሆኑ የሰብዓዊ መብት አጀንዳዎችን በአራት በመክፈል፣ ከአሥራ አንዱ ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች አንደኛው […]