የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎች የሀገራዊ ምክክሩ ባለቤት በመሆን ሙያቸውን ለዚህ ታሪካዊ ሁነት እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀረበ

sf

የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎች የሀገራዊ ምክክሩ ባለቤት በመሆን ሙያቸውን ለዚህ ታሪካዊ ሁነት እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀረበ

 

ግንቦት 11/2017 ዓ.ም

 

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዲጂታል (ማህበራዊ) ሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

 

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የደረሰበትን ደረጃ በሚመጥን መልኩ ዲጂታል ሚዲያው ሂደቱን በመደገፍ ትልቅ አስተዋፅኦ ሊያደርግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

 

በሀገራችን ያሉ የዲጂታል ሚዲያዎች የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን በሚያግዝ እና በሚጠቅም መልኩ መጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

 

የዲጂታል ሚዲያው በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ላይ ሊኖረው በሚገባው ሚና ላይ የውይይት መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር)ኮሚሽኑ በአሁን ሰዓት እየተንቀሳቀሰ የሚገኝበትን የሀገራዊ ምክክር ዓውድ አስረድተዋል፡፡

 

የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎች የሀገራዊ ምክከሩ ባለቤት በመሆን ሙያቸውን እና ዕውቀታቸውን ለዚህ ታሪካዊ ሁነት እንዲያበረክቱም ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

ሂደቱ በማናቸውም ሀይሎች እንዳይጠለፍ የባለቤትነት ሚናቸውን በመወጣት የበኩላቸውን እንዲወጡም ነው ያስገነዘቡት፡፡

 

የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎች የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን የሚያግዙ የአብሮነት ትርክቶችን በማዘጋጀት ለምክክር ሂደቱ አስቻይ ሁኔታን መፍጠር እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡

 

በመድረኩ ኮሚሽኑ በእስካሁኑ ጉዞው ያከናወናቸው አበይት ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮች፣ የተወሰዱ የመፍትሔ ሀሳቦች እና ቀሪ ተግባራት ለውይይቱ ተሳታፊዎች ቀርቧል፡፡