ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም
በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኦሮሚያ ክልል የህብረተሰብ ክፍሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ዛሬ ለአራተኛ ቀን ቀጥሎ እየተደረገ ነው።
በዛሬው ዕለት በቀጣይ የምክክር ሂደቶች የሚሳተፉ ተወካዮች ከአሥሩም የህብረተሰብ ክፍሎች እየተመረጡ ነው።
የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ምርጫ በእያንዳንዱ የክላስተር ቡድን ደረጃ የሚከናወን ነው።
እያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል በክላስተር ደረጃ 8 ተወካዮችን በሚስጥራዊ መንገድ ይመርጣል።
በአንድ ክላስተር 80 ተወካዮች ሲመረጡ፤ አንድ የህብረተሰብ ክፍል በክልል ደረጃ 32 ተወካዮች ይኖሩታል።
በኦሮሚያ ክልል አሥሩን የወረዳ የማህበረሰብ መሰረቶችን ወክለው አጀንዳ የሚያጠናቅሩ 320 ተወካዮች ይኖራሉ።
የወረዳ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርጉት የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ደግሞ ከመጪው እሁድ ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም ጀምሮ ይከናወናል።