የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የትውውቅና የምክክር መድረክ በጂጂጋ ከተማ አካሄደ፡፡

የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች መካከል በአምባሳደር ሙሃሙድ ድሪር፣ በዶ/ር ዮናስ አዳዬ እንዲሁም በዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ የተመራው ቡድን ወደ ሶማሌ ክልል ዋና መቀመጫ ጂጂጋ ከተማ አቅንቶ ከክልሉ መስተዳድር እና የካቢኔ አባላት ጋር የትውውቅ እና ውይይት መድረክ አከናውኗል፡፡

መድረኩም  የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር በአምባሳደር ሙሃሙድ ድሪር ስለ ጉብኝታቸው ዕቅድ አጠር ያለ ማብራሪያ ካቀረቡ በኃላ ስለ ኮሚሽኑ አመሰራረት፣ አላማ እና ተግባራት ገለፃ ሰተዋል፡፡ በመቀጠልም ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ስለ ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ሰፊ ገለፃ የሰጡ ሲሆን በተለይም የሀገራዊ ምክክሩ መርሆዎች ጥልቅ የሆነ ገለፃ አድርገዋል፡፡ እንዲሁ ኮሚሽነር ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ ኮሚሽኑ እስካሁን የሰራቸውን ስራዎች፣ ወደፊት ስለሚሰራቸው ተግባራት፣ ወደፊት ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብለው በተገመቱ ተግዳሮቶች ላይ እና የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች የስራ ክፍፍል ላይ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል

ምክክሩየሚደረገው በብሔራዊ ደረጃ ነው ወይስ በክልል ደረጃ ወይንስ በሁለቱም? ምክክሮቹ የሚደረጉት በተመሳሳይ ጊዜ ነው ወይንስ ቅደም ተከተል አለው? ምክክሩ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማለትም ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ማደራደርን፣ ማስማማትን ያካትታል?

በአሁን  ጊዜ ኢትዮጰያ እያጋጠማት ካለው አለመረጋጋት እና ግጭት አንፃር አሁን ላይ ሀገራዊ ምክክር ማደርግ ትክክል ነው ወይም ያስኬዳል ብላቹህ ታስባላቹህ? አሁን ላይ ከሚስተዋሉት ማዕከላዊነት/አሃዳዊነት እና ፌደራሊስት አስተሳሰቦችን እንዴት ልታቀራርቡ አስባችል? ወይንም ይሄን ነባራዊ ሁኔታ ለመዋጋት የሚያግዝ መንገድ/ ስልት አለ?ሀገራዊ ምክክሩን መቼ ልታጠናቅቁ አቅዳችል? የተዘጋጀ ፍኖተካርታ አለ ወይ? ምክክሩ ላይ እንዳይቀርቡ በቀይ መስመር ያስቀመጣቹኋቸው አጀንዳወች አሉ ወይ? አንዱ የምክክሩ መርህ “ግልጽኝነት” ነው፡፡ እና ምን ያህል ተግባራዊ ታደርጉታላቹህ በሁሉም ደረጃ?ሀገራችን የተገነባችው በውሸት እና በሃይል ነው፡፡ ምክከር ኮሚሽኑ ይሄን ክፍተት እንዴት ያስታርቀዋል?

ከላይ በዝርዝር ቀረቡት ሃሳቦች በመድረኩ የተንፀባረቁ ሲሆን ከኮሚሽን አባላትም ግብረመልስ ተሰቶባቸዋል፡፡ ከግብረመልሱ በኃላ አብሮ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ውይይት ተደርጎ የትውውቅ መድረኩ መዝጊያ ሆኗል፡፡