የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትውውቅና የምክክር መድረክ በባህር ዳር ከተማ አካሄደ፡፡

endc bahirdar

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ውጤታማ እንዲሆን የአማራ ክልል መንግሥት ድጋፍ ያደርጋል” – ዶ/ር ይልቃል ከፋለ
የግጭት መነሻ የሚሆኑ ልዩነቶችን በውይይት የመፍታት ባህላችን ሊጎለብት ይገባል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ገለፁ።

 

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት ከአማራ ክልል መንግሥት የካቢኔ አባላት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከወጣቶች ተወካዮች ጋር ትውውቅ እያደረጉ ነው።

 

በትውውቅ መድረኩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እንደገለፁት፥ ችግሮችን በውይይት እና በምክክር የመፍታት ባህላችንን ማጎልበት አለብን ብለዋል።

 

የኢትዮጵያውያን አንድነት ተጠናክሮ መውጣት ግድ የሚልበት ወቅት ላይ እንገኛለን ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ይህ እውን ይሆን ዘንድ ልዩነቶችን በሰለጠነ እና በሰከነ መንፈስ በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

 

የአማራ ህዝብ ያሉት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያ ጥያቄዎች በውይይት የሚመለሱ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

 

ኮሚሽኑ ውጤታማ እንዲሆን መላ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር ሊያደርጉ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

 

የሚያለያዩ ነገሮች ቢኖሩ እንኳ እነሱን አቻችሎ መኖር የሚቻልበት ስርዓት መፍጠር ይገባል ብለዋል።

 

የአማራ ክልል መንግሥት ኮሚሽኑ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅበትን እንደሚወጣም ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።

 

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ሀገራዊ ምክክሩን በአግባቡ ማስኬድ እንዲችል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመንቀሳቀስ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ትውውቅ እና ውይይት እያደረገ ነው ብለዋል።

 

ስለኮሚሽኑ አመሰራረትና ስላሉት ኃላፊነቶችም ፕሮፌሰር መስፍን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

 

ልዩነትን በማጥበብና በመቻቻል የተመሠረተች ጠንካራ ሀገር እንድትኖር የአማራ ክልል መንግሥት ከሀገራዊ ምክክሩ ጎን በመኾን አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

 

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጋር የትውውቅ መርኃግብር አካሂደዋል።

 

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌ ተወካዮች፣ እናቶች እና ወጣቶች በተገኙበት የትውውቅ መርኃግብር አካሂዷል።በመድረኩ ላይ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እና ሌሎች አባላትም በመድረኩ ተገኝተዋል።የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) “አንድ ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ሀገራዊ ችግሮቻችንን በምክክርና በመነጋገር መፍታት ያስፈልጋል”ብለዋል።

 

ልዩነትን በማጥበብና በመቻቻል የተመሠረተች ጠንካራ ሀገር እንድትኖር የአማራ ክልል መንግሥት ከሀገራዊ ምክክሩ ጎን በመኾን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ርእሰ መሥተዳድሩ ገልጸዋል።

 

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር) ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የልዩነትን አጀንዳዎች ለመቀነስ እና አንድነትን ለማጠናከር አልሞ የተቋቋመ መኾኑን ተናግረዋል።

 

“የሀገራችን ሕዝቦች ላያግባቡ የቻሉ ጉዳዮችን ነቅሰን በማውጣት እንድንወያይባቸው እና የጋራ መግባባት ላይ እንድንደርስ አልመን እየሠራን ነው” ብለዋል። በዚህ ኹሉ ሂደት ውስጥ ኹሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ እኩል መሳተፍ እንዳለባቸውም ተናግረዋል።