የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን የመጀመሪያ ውይይት በመቀሌ ከተማ አካሄደ፡፡

tigray

በኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የተመራውና ሌሎች 4 ኮሚሽነሮችን ያካተተው የኮሚሽኑ ልዑካን ቡድን ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ መቀሌ ጉዞውን አድርጎ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡

ኮሚሽኑን ወክሎ የተጓዘው ቡድን ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እና ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ጋር ተገናኝቶ የተወያየ ሲሆን በቀጣይ በክልሉ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶችን ለመተግበር የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ አሰራር ኮሚሽኑ መተግበር እንደሚገባው ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በውይይቶቹም ላይ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት ገላፃ አድርገው ከእነዚህ ባለድርሻ አካላት ሊደረግላቸው የሚገቡ ትብብሮችን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም ኮሚሽኑ በክልሉ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ደረጃ በደረጃ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ማከናወን እንደሚገባው በውይይቱ የተመላከተ ሲሆን የክልሉ መንግስት ኮሚሽኑ ለሚያከናውናቸው ተግባራት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡