የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የባለድርሻ አካላት ትብብር ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ወሳኝ ነው- ኮሚሽኑ

img 20250507 181135 488

የባለድርሻ አካላት ትብብር ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ወሳኝ ነው- ኮሚሽኑ

ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደትን የተመለከተ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በዚህ አውደ ጥናት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር መሀሙድ ድሪር የባለ ድርሻ አካላት ትብብር እስካሁን በነበረው የምክክር ሂደት ያጋጠሙ ውጣ ውረዶችን ለማለፍ ጉልህ እገዛ ማድረጉን አንስተዋል።

ይህ በጋራ ጉዳይ አብሮ የመስራት ባህል በቀጣይ ለሚከናወኑ የምክክር ሂደቶችም ወሳኝ እንደሆነ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው በአመለካከትና በሀሳብ የተራራቁ አካላትን አሰባስቦ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ማድረግ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።

ምክክር እውነትን የምንፈልግበት መንገድ ነው ያሉት ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) አንዱ የአንዱን ችግር የሚረዳው ምክክር ሲያደርግ ብቻ ነው ሲሉም አክለዋል።

አውደ ጥናቱን የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ያዘጋጀው ሲሆን በመድረኩም የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡