የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የሀገራዊ ምክክር መረጃዎች

የሀገራዊ ምክክር የሂደት ምዕራፎች

hidet

በምክክር ሂደት ያለፉ በርካታ ሀገራት በአብዛኛው ሦስት የሂደት ምዕራፎችን ተከትለዋል፡፡ የዝግጅት፣ የምክክር ሂደት እንዲሁም ትግበራና ክትትል፡፡ በኢትዮጵያ በሂደት ላይ ላላው ሀገራዊ ምክክር በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ምዕራፎቹ አራት ሆነዋል፡፡

በቂ ቅድመ ዝግጅት

የሀገራዊ ምክክርን ጽንሰ ሀሳብ በመረዳት፣ በማጥናት እና በመዘጋጀት በቂ ጊዜ መወሰዱ ለሂደቱና ለሚያስገኘው ውጤት መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ቀረጻ፣ የተሳታፊ ልየታና መሰል ተግባራት በቂ ጊዜ ተወስዶ በጥንቃቄ ካልተሰሩ፣ በህብረተሰቡ ዘንድ ተዓማኒነቱ የተጠናከረ ካልሆነ፣ ባለድርሻ አካላትን በየሂደቱ አካቶ ማሳተፍ እና ቁርጠኝነትን ማጎልበት ካልተቻለ ሂደቱ የተበላሸ፣ ውጤቱም አመርቂ አይሆንም፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ወደ ዝግጅት ምዕራፉ ከመገባቱ በፊት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አከናውኗል፡፡ በዚህም በአዋጁ መሠረት አስራ አንዱ ኮሚሽነሮች በየካቲት 14 2014 ዓ.ም እንደተሰየሙለት በየካቲት 16 2014 ዓ.ም ስራዉን ጀምሯል፡፡ ከዚሁ በተጓዳኝም ኮሚሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማ፣ የተሰጡትን ተግባራትና ሀላፊነቶች እንዲሁም የሚጠበቁበትን ውጤቶች በተመለከተ የአዋጁን ይዘትና አውድ በአግባቡ ለመረዳት ሰፊ ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚህም አዋጁን በማርቀቅና በማጽደቅ ሂደት ዋነኛ ተዋናይ ከነበሩ የፍትህ ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ምክክር ተደርጓል፡፡

ምንም እንኳ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ በዚህ ስፋትና ጥልቀት ልክ ሀገራዊ ገጽታ ተሰጥቶት ሲካሄድ አዲስ ቢሆንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰፊ ተሞክሮ ያለው እንደመሆኑ መጠን የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ጥናትና ምርምርን መሠረት አድርገው የተዘጋጁ ሰነዶችን በማገለባጥ የተሻለ መረዳት እንዲኖር ጥረት ተደርጓል፡፡ የስራውን ስፋትና ጥልቀት መረዳትን ተከትሎም ለዚህ የሚመጥን ተቋማዊ ቁመናን በሂደት ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡

 

የኮሚሽኑ ዋና መቤት
የኮሚሽኑ ዋና መ/ቤት

የዝግጅት ምዕራፍ በራሱ መለሰተኛ የምክክር ሂደት ነው፡፡

ሀገራዊ ምክክሩ ከመጀመሩ በፊት የዝግጅት ሂደቱ ረዘም ያለ ጊዜና የራሱ የሆነ ተቋማዊ መሠረተ ልማት ይፈልጋል።

  • ሀገራዊ ምክክሩ ምን አይነት ይዘትና ቅርጽ ይኑረው?
  • በሂደቱ ውስጥ የትኞቹ አካላት ናቸው መሳተፍ ያለባቸው?
  • በምን ያህል መጠንና ተካታችነት?
  • ምክክር የሚደረግባቸው አጀንዳዎች በምን መልክ ተሰባስበው ይቀረጹ?
  • ለምክክር ሂደቱ ስኬት አጋዥ የሆኑ አካላት የትኞቹ ናቸው?
  • በምን አይነት ማዕቀፍ ውስጥስ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይችላሉ? ለሚሉትና መሰል አንኳር ጉዳዮች ምላሽ ለመስጠት ጥረት የሚደረግበት ምዕራፍ ነው፡፡ እነዚህ ጉዳዮች የሚወሰኑት በሂደቱ ዓላማ፣ ባለው የፋይናንስ አቅም እና በዋና ባለድርሻ አካላት ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ነው፡፡

ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ያከናወናቸው አበይት ተግባራት እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

ሀ. የመፈጸም አቅምን መገንባት

ሀገራዊ የምክክር ተግባሩ ገለልተኛና ራሱን በቻለ ተቋም እንዲመራ መደረጉ ለምክክር ሂደቱ መሳካት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሂደቱን የመምራትና የማስፈጸም የቤት ስራ የተሰጠው ተቋም አስቀድሞ ያልተፈጠረና ያልተደራጀ እንደመሆኑ መጠን ተቋማዊ ቅርጽ ለማስያዝ ሰፊ ጥረትን ጠይቋል፡፡ በዚህም አስራ አንዱ ኮሚሽነሮች በአራት ቡድኖች (Pillars) እንዲዋቀሩና በስራቸውም አስፈላጊ ባለሙያዎችን በማካተት የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹ እንዲከናወኑ ተደርጓል፡፡ በኮሚሽኑ የእስካሁን እንቅስቃሴ ሂደቱን ለመምራት የሚያስችል የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ተዘጋጅቶና በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ዳብሮ እንዲጸድቅ በማድረግ ወደ ስራ መገባቱ ተጠቃሽ ነው፡፡

የኮሚሽኑ የሦስት ዓመት ረቂቅ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ላይ የባለድርሻ አካላት አስተያየትና ግብዓት ሲሰባሰብ
የኮሚሽኑ የሦስት ዓመት ረቂቅ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ላይ የባለድርሻ አካላት አስተያየትና ግብዓት ሲሰባሰብ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መዋቅር

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መዋቅር

የዘርፎች ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት

  • ዋና ኮሚሽነር ጽ/ቤት

አጠቃላይ አመራር የሚሰጥና አስተዳደራዊ ስራዎችን የሚያከናውን ነው፡፡ ቡድኑ በዋናነት ተቋማዊ ግንባታ እና የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ላይ በማተኮር ስራዎችን እንዲሰራ ሀላፊነት የተሰጠው ነው፡፡

  • የአጀንዳ ቀረጻና ምክክር ዘርፍ

ሀገራዊ ምክክሩን ለማካሄድ አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት፣ የሂደትና የትግበራ ስራዎችን በትኩረት የሚሰራ ነው፡፡ የተሳትፎና አካታችነት፣ የአጀንዳ ማሰባሰብና ቀረጻ እንዲሁም አጠቃላይ የምክክር ሂደቱን በአግባቡ የመሰነድ ስራዎችን ያከናውናል፡፡

  • የጥናት፣ የአሰራር ስርዓቶችና ስልጠና ዘርፍ

በአቅም ግንባታ እና በጥናትና ምርምር ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ነው፡፡ በዚህም የስልጠና፣ የጥናትና ምርምር፣ የአወያዮችና አመቻቾች ምልመላ፣ ስልጠናና አስተዳደር እንዲሁም መሰል ተግባራትን በማከናወን ተቋማዊ አቅምን በማጠናከርና የአሰራር ስርአቶችን በመዘርጋት ተግባራዊ እዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡

  • የሚዲያ፣ ኮሙኒኬሽንና አጋርነት ዘርፍ

የሚዲያ ኮሚኒኬሽንና የአጋርነት ስራዎችን የሚያስተባበር ቡድን ነው፡፡ ቡድኑ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ስራዎችን በመስራት በሀገራዊ ምክክር ጽንሰ ሀሳብና ሂደቶች ላይ ግንዛቤ የመፍጠር፣ የተቋሙን ገጽታ በመገንባት ተአማኒነቱንና ተቀባይነቱን የማሳደግ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውጤታማ ትብብሮች እንዲኖሩ ለማስቻል ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡

  • አማካሪ ኮሚቴ

የኮሚሽኑን ምክር ቤት በማማከር ከፍተኛ እገዛ የሚያደርጉ 35 አባላት ያሉት ኮሚቴ ነው፡፡ አባላቱ ባለቸው ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት፣ የህዝብና የባለድርሻ አካላት ሰፊ ተቀባይነት፣ ባከባተቱት ሰፊ የስራ ልምድ እንዲሁም የምክክሩ ሂደት እንዲሳካ ባላቸው ቀናኢነት ከመላው ኢትዮጵያ የተመለመሉ ናቸው፡፡ የሀይማኖትና የማህበረሰብ መሪዎች፣ ከፍተኛ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች እንዲሁም በተለያዩ የሙያ መስኮች የካበተ ልምድ ያላቸው ዜጎችን ተካተዋል፡፡

የኮሚሽኑ አማካሪ ኮሚቴ አባላት በከፊል
የኮሚሽኑ አማካሪ ኮሚቴ አባላት በከፊል

ለ. መመሪያዎችንና ግልጽ የአሰራር ስርዓቶችን መዘርጋት

ለሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት ቁልፍ ከሆኑ ተግባራት አንዱ እንደመሆኑ መጠን በዚህ በዝግጅት ምዕራፍ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ በዚህም ከአጀንዳ ቀረጻ ጀምሮ ባለው ሂደት ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮች አካታች በሆነ መልኩ የሚለዩበት እና አጀንዳ ማሰባሰብ የሚካሄድባቸውን ስርአቶችና ስልቶች በጥንቃቄና ዝርዝር ጉዳዮችን ባከተተ መልኩ ለማዘጋጀት ሰፊ ጥረት ተደርጓል፡፡

በምክክር ሂደቱ የሚሳተፉ የማህበረሰብ ክፍሎችን የመለየቱና አጀንዳ የማሰባሰበ ሂደት ምን ቢሆን ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንደሚቻልም በተለያዩ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ሰፊ ውይይቶች ተደርገው ጠቃሚ ግበዓት ተወሰዶባቸዋል፡፡

በተሳታፊ ልየታ የአሰራር ሥርዓት ወይም ሥነ ዘዴ ዝግጅት ወቅት ከተያዩ ባለድርሻ አካላት ግብዓት የማሰባሰቢያ መድረኮች

በሲዳማ ክልል-ሐዋሳ ከተማ

በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ

በኦሮሚያ ክልል-አዳማ ከተማ

በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ

በቀድሞው የደቡብ ብሄር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልል – አርባ ምንጭ ከተማ በቀድሞው የደቡብ ብሄር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልል አርባ ምንጭ ከተማ

በኦሮሚያ ክልል – ጅማ ከተማ

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ

በአማራ ክልል – ጎንደር ከተማ

በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ

በአማራ ክልል – ደሴ ከተማ

በአማራ ክልል ደሴ ከተማ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ – ቦንጋ ከተማ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቦንጋ ከተማ

የሱማሊና ሐረሪ ክልሎች

የሱማሊና ሐረሪ ክልሎቸ

ከአፋር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ከመጡ ተሳታፊዎች

ከአፋር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ከመጡ ተሳታፊዎች

ሐ. ከባለድርሻ አካላት ጋር አጋርነትን መፍጠር

በመለየት በጉዳዩ ላይ ከመመካከር ባለፈ የመግባበያ ስምምነቶችን ለማድረግ ሰፊ ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚህም ከፌደራልና ከክልል መንግስታት፣ ከሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፣ ከሀገር አቀፍ የዕድሮች ጥምረት፣ከሲቪክ ማህበራት፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሚዲያ አካላት እና ከሌሎችም ጋር በጋራ ለመስራት የተደረሱ መግባባቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሰላም እናቶች ጋር የጸሎትና የምርቃት መርሐ ግብር
ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሰላም እናቶች ጋር የጸሎትና የምርቃት መርሐ ግብር
የሱማሊ ክልል መስተዳደር፣ የሲቪክ ማህበራት ጥምረት እና የሶማሊ የሀገር ሽማግሌዎች ካውንስል ጋር
የሱማሊ ክልል መስተዳደር፣ የሲቪክ ማህበራት ጥምረት እና የሶማሊ የሀገር ሽማግሌዎች ካውንስል ጋር
አዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሐይማኖት ማህበራት፣ አካል ጉዳተኞች... ጋር
አዲስ አበባ- የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሐይማኖት ማህበራት፣ አካል ጉዳተኞች… ጋር
ከመገናኛ ብዙኃን ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር
ከመገናኛ ብዙኃን ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር
ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም እና ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር
ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም እና ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጋር
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጋር

የሂደት ምዕራፍ

ይህ ምዕራፍ “ፈጥነህ ለመድረስ በዝግታ ተራመድ” (Go slow to go fast) በሚል መርህ የሚመራ ነው፡፡ “ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል” የሚባለው ሀገርኛ ቢሂልም ይገልጸዋል፡፡ አገላለጾቹ ምክክር ሂደት እንደመሆኑ መጠን እርጋታና ጥንቃቄ እንዲሚያስፈልገው አድምቀው የሚያሰመሩ ናቸው፡፡ የሂደት ምዕራፍ የሀገራዊ ምክክሩ የህዝብ ባለቤትነት ጎልቶ የሚወጣበትም ምዕራፍ ነው።

ቀደም ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው እያንዳንዱ የምክክር ምዕራፍ የየራሱ ቅድመ ዝግጅት አለው፡፡ አንዳንድ ወገኖች ይህንን ባለመረዳት ወይም የምክክር ሂደቱ ተፋጥኖ ለሚያስገኘው ውጤት በመጓጓት ኮሚሽኑ ስራውን እንደጀመረ በጥቂት ወራት ምክክሩ እንደሚካሄድ መጠበቃቸውን መገንዘብ ይቻላል፡፡ በዚህኛውም ምዕራፍም ቢሆን በቀጥታ ወደ ምክክሩ እንደሚገባ ሊገምቱ ይችላሉ፡፡

ሆኖም ውጤታማ ለመሆን በቂ ዝግጅት አስፈላጊ በመሆኑ ይህኛውም ምዕራፍ በራሱ ዝግጅት የሚካሄድ ነው፡፡ በመሆኑም ምክክሩ ተካሂዶ የሚያስገኛቸውን ውጤቶች በመጠበቅና ሂደቱ የሚያስፈልገውን ጥንቃቄ ከሚዛን ውስጥ ማስገባት ተገቢ ይሆናል፡፡

በዚህ ምዕራፍ መመሪያዎችንና እና ውስጠ ደንቦችን ማዘጋጀት፣ የአሰራር ስርዓቶችን መዘርጋት፣ የተሳትፊ ብዛትን መወሰን ፣ ተሳታፊዎችን መለየትን፣ ምክክር የሚደረግባቸውን የአጀንዳ ሀሳቦችን ማሰብሰብ፣ የምክክር አወያዮችን (moderators) መለየትና ማዘጋጀት፣ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የህዝብን ተሳትፎ ማጠናከር፣ የድጋፍ አወቃቀሮችን መፍጠር፣ የምክክሩን ሂደት ቅርቃር ውስጥ ሊከቱ የሚችሉ ማነቆዎችን የመፍቻ ስልቶችን ማዘጋጀት/ Dead Lock Mechanisms/ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ለምክክሩ አስፈላጊ የሆኑ አንጻራዊ ሰላማዊና ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ናቸው፡፡ የተወሰኑትን ገባ ብለን ቀጥለን እንመለከታለን፡፡

ሀ. የአሰራር መመሪያዎችንና የሥነ -ምግባር ውስጠ ደንቦችን ማዘጋጀት

ሀገራዊ ምክክሮች የሚመሩት የሂደቱን መርሆዎች መሠረት በማድረግ ነው። እነዚህን መርሆዎች በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድግ የተለያዩ መመሪያዎችና የሥነ ምግባር መመሪያዎች ተዘጋጅተው መተግበር ይኖርባቸዋል፡፡ በምክክር ሂደቱ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮችና ሌሎች ሰራተኞች እንዲሁም ምክክሩን እንዲያመቻቹ ወይም እንዲመሩ የሚመረጡ ሰዎች ሊኖሯቸው የሚገቡ ሥነ- ምግባሮችና መከተል ያለባቸው የአሰራር ሂደቶችን በተመለከተ ግልጽና ሊተገበር የሚችል መመሪያ ሊዘጋጅ ይገባል፡፡ ይህም በተለያየ አከባቢ፣ ባህል፣ ቋንቋና ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ውስጥ የሚካሄዱ ምክክሮች ወጥ በሆነ ስታንዳርድ እንዲካሄዱ ለማድረግ ይረዳል፡፡ እነዚህ ተግባራት የምክክሩን ሂደት ፍትሃዊነትና ቅቡልነትን ለማጎልበት ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው፡፡ 

መመሪያዎች ተዘጋጅተው መተገብራቸው ተሳታፊዎች የሚያደርጉት ምክክር አክብሮት የተሞላበትና መደማመጥ የሰፈነበት እንዲሁም የህብረተሰቡ እና የሌሎች ባለድርሻ አካላት እምነት የሚያሳድሩበት እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ የምክክር ሂደቱን በትክክለኛው መንገድ ላይ በማቆየት በመካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በመፍታት ወደ ውጤት እንዲያመራ ለማድረግም ይረዳሉ፡፡ የአሰራር መመሪያዎቹ በምክክር ሂደቱ ለሚሳተፉ አካላት ሁሉ በግልጽ እንዲረዱትና ስምምነት ላይ እንዲደርሱባቸው ማድረግም አስፈላጊ ነው፡፡  

ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ልዩ ልዩ መመሪያዎችንና ውስጠ ደንቦችን በማዘጋጀት ተግባራዊ እንዲያደርግ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በዋናነትም የምክክር ሂደቱ መሰረታዊ ጉዳዮች ማለትም የአጀንዳ ማሰባሰብና ቀረጻ፣ እንዲሁም አካታች የሆነ ሰፊ ተሳትፎን ለማረጋገጥና የምክክሩን ሂደት ለመምራት የሚያስችሉ መመሪያዎችን የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍና ግብአቶችን በመውሰድ አዘጋጅቷል፡፡

ለ. የተሳታፊዎችን ብዛት መወሰን

የተሳታፊዎች መጠን በሚካሄደው ምክክር ለማሳካት እንደሚፈለገው ግብና ዓላማ የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክክሩ በመሰረታዊ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በመመካከር ከሀገራዊ መግባባት ላይ ለመድረስና አዲስ የማህበራዊ ውል ለመፍጠር የሚደረግ ከሆነ የተሳታፊዎቹ መጠን ሰፊና የታችኛውን የማህበረሰብ ክፍል የሚያካትት መሆን ይኖርበታል፡፡

በኢትዮጵያ የሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር ዓለማ በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያሉ አለመግባባቶችን በምክክር ሂደት ወደ መግባባት ማምጣትና አዲስ የፖለቲካ ባህል መፍጠር እንደመሆኑ መጠን አቅም የፈቀደውን ያህል ሰፊውን ማህበረሰብ በበቂ መጠን ማሳተፍ ይጠበቅበታል፡፡ ይህም ሆኖ ሁሉንም ለምከክሩ ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማሳተፍ የሚቻልበት እድል ጠባብ በመሆኑ የውክልና አሰራርን ተግባራዊ ማድረጉ ተመራጭ ነው፡፡ 

በመሆኑም የምክክር ኮሚሽኑ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የተሳታፊዎች ብዛት የምክክር ሂደቱ አካታች ግልጽ እና ለትግበራ ምቹ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን ያከናውናል፡፡ በውክልና ከሚሳተፉ ዜጎች በተጨማሪ በተለያዩ የመሳተፊያ አማራጮችን በማመቻቸት ጭምር ህዝቡ የምክክሩ ሂደት ተሳታፊና የውጤቱም ባለቤት እንዲሆን ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

ከዚህ አኳያ በመላው ኢትዮጵያ ከወረዳ ጀምሮ ያሉ መዋቅሮችን በመለየት ከእያንዳንዱ ወረዳ ማህበረሰቡ ለምክክሩ ይወክሉኛል የሚላቸውን ተሳታፊዎች የሚመርጥበት ስርአት ዘርግቷል፡፡ የአጀንዳ ማሰባሰብና የምክክር ሂደቱም በሁሉም ክልሎች፣ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በፌደራል ደረጃ ለማካሄድ የሚያስችሉ አሰራሮች ተዘርግተዋል፡፡ በዚህም ሳይወሰን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዲያስፖራ የማህበረሰብ አባላትም በምክክሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

miraf 03

 

በወረዳ ደረጃ በአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ የሚሳተፉ ተሳታፊዎችን የሚወክሉና በመድረኩ የሚሳተፉ ተወካዮች ልየታ የደረሰበት ደረጃ በወረዳ ደረጃ በአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ የሚሳተፉ ተሳታፊዎችን የሚወክሉና በመድረኩ የሚሳተፉ ተወካዮች ልየታ የደረሰበት ደረጃ 02

የሀገራዊ ምክክር ምክረ ሀሳቦችና አተገባበር

ምክረ ሀሳቦችና አተገባበር

የሀገራዊ ምክክር ውጤቶችን በአግባቡ መረዳት፣ የተገኙ ውጤቶች ተግባራዊ የሚሆኑበትን ዝርዝር ዕቅድ ማዘጋጀትና ስልቶችን መንደፍ እንዲሁም ለትግበራው ምዕራፍ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት አተገባበሩን መከታተል ትኩረት የሚሰጣቸው አንኳር ጉዳዮች ናቸው፡፡

ሀገራዊ ምክክር ትልቅ የሽግግር ፍኖተ ካርታ አካል ሆኖ በኢኮኖሚ፣ በመዋቅራዊ፣ በፖለቲካ እና በፍትህ ማሻሻያ ሂደቶች መታጀብ አለበት። ሀገራዊ ምክክሮች በራሳቸው ፍጻሜ ሳይሆኑ የተቀናጀና አሳታፊ የለውጥ ሂደት ጅምር መሆናቸው መታወቅ አለበት።

 

የምክክር ሂደት የመጨረሻው ምዕራፍ በምክክሩ መግባባት የተደረሰባቸውን ምክረ-ሀሳቦች ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ እንደ ምክረ-ሀሳቦቹ ባህርይ ተግባራዊነታቸው በአጭር፣ በመካከለኛ ወይም በረዥም ጊዜ ተፈጻሚ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የሚተገበሩበት ፍጥነትና ስፋት እንደ ምክረ-ሀሳቦቹ ባህርይ ብቻም ሳይሆን ለተግባራዊነቱ ባለድርሻ የሆኑ አካላት እንደሚያደርጉት ጥረትና እንደሚኖራቸው ቁርጠኝነትም ሊለያይ ይችላል፡፡

የሚደረገው ጥረትና የሚኖረው ቁርጠኝነት ከፍተኛ ሲሆን፡ በአጠረ ጊዜና በምልዓት ተግባራዊ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ የተግባራዊነቱን ሰፋትና ፍጥነትን የመወሰን አቅም ያለቸው በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም በዋናነት ግን መገባባት ላይ የተደረሰበት መንገድ፣ አሳታፊነቱ፣ አካታችነቱና ግልጸኝነቱ ወሳኝ መነሻዎች ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር ሂደቱ ቅቡልነት ያለውና መሠረተ ሰፊ የሆነ መግባባት ላይ ከተደረሰ አተገባበሩ ሰፊና ፈጣን የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ የአስፈጻሚውን አካል የቤት ስራም ቀላል ያደርገዋል፡፡ በሌላም መልኩ አስፈጻሚው አካል የሕዝቡን ፍላጎት ተረድቶና አክብሮ ተግባራዊ እንዲያደርግ ተጽእኖ የመፍጠርን ጉልበት ያገኛል፡፡ ይህም በመሆኑ ነው በሀገራዊ ምክክር ላይ ከውጤቱ ይልቅ ሂደቱ ጤናማ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት መደረግ ያለበት፡፡

ሀገራዊ ምክክሮች ከመመካከር ሂደት ባሻገር በተግባር ላይ በሚውሉ መርሆች ላይ ተመስርተው የሚመቻቹ ሂደቶች ናቸው። የትግበራው ምዕራፍ የተለያዩ ተግዳሮቶችን እና ዕድሎችን ይዞ የሚመጣ ነው፡፡ በምክክር ሂደት ላይ መሳተፍ በራሱ የሚያመጣቸው ማህበራዊ በበጎ ልምምዶች እንደተጠበቁ ሆነው መግባባት ላይ የተደረሰባቸው ሀሳቦች ወደ ተግባር ተለውጠው መታየት ይኖርባቸዋል፡፡

በወቅቱ ከተፈጠሩና መሰረታዊ ልዩነቶች ናቸው ተብለው በምክክር ሂደት መግባባት ከተደረሳበቸው አጀንዳዎች በተጨማሪ ቀሪ ጉዳዮችን ወይም በቀጣይ ሊፈጠሩ የሚችሉ አዳዲስ የልዩነት ሀሳቦችን ቀጣይነት ባለው የምክክር ሂደት ለመፍታት እንዲቻል ለቀደመው ሀገራዊ ምክክር ተገቢውን ዋጋና ክብር በመስጠት የተደረሰባቸው መግባባቶች ተግባራዊ እዲሆኑ መደረግ አለበት፡፡

በምክክር ሂደቱ መግባባት ላይ መደረሱን እንደ መጨረሻ ውጤት በመውሰድ የሚመለከታቸው ወሳኝ ባለድርሻ አካላት ትኩረታቸውን እንዳይቀንሱ የሚያደርጉ ተግባራት አስቀድመው መታቀድና በየወቅቱ እና በየደረጃው መከናወን ይኖርባቸዋል፡፡ በመሆኑም ለተፈጻሚነታቸው ዝርዝር የአፈጻጻም ዕቅድ ማዘጋጀት፣ ህዝቡና ባለድርሻ አካላት በቂ ግንዛቤ አግኝተው በሂደቱ እንዲቀጥሉበት መበረታታት እንዲሁም በሂደቱ የተገኙ የመከባበር፣ የመተባባርና የመተማመን ተሞክሮዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያደርጉ ስራዎች ቀጣይነት ሊኖራቸው ይገባል፡፡

በጥቅሉ የሀገራዊ ምክክሮች ውጤቶች በሁለት ተከፍለው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ተጨባጭ (tangible) እና የማይዳሰሱ (intangible)፡፡ ተጨባጭ የሆኑ ውጤቶች ምክክር በተደረገባቸው አጀንዳዎች ላይ የተደረሰባቸው መግባባቶች ናቸው፡፡ በስምምነቶች፣ በሪፖርት ወይም በመግለጫ እና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ምክረሃሳቦችን በማካተት ሊገለጹ ይችላሉ።

የሀገራዊ ምክክር ሂደት ተጨባጭ ውጤቶች በተቋማዊና “በሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ” ፣ በፖለቲካ፣ በፍትሕ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችና ግንባታዎች ዙሪያ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ ምክረ ሀሳቦችን ያካትታሉ። ሁለተንናዊ ለሆነ አዲስ ለውጥ ፍኖተ ካርታ የመሆን አቅምም አላቸው፡፡ ተጠባቂው ውጤት እንደየሀገራዊ ምክክሩ አላማዎች የተለያየ ነው፡፡ በአንዳንድ ሀገራት በተደረጉ ሀገራዊ ምክክሮች ህገ መንግስታዊ ለውጥ፣ የአዲስ መንግስት ምስረታ ወይም የስልጣን ክፍፍል፣ የሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበር፣ የሰላም መስፈን፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሪፎርሞች እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህን አስገኝተዋል፡፡

ከማይዳሰሱ የምክክር ሂደት ውጤቶች መካካል በተለያዩ ባለድርሻ አካላት መካከል የግንኙነቶች ለውጥ እና በቀጣይነት ሊጠናከር የሚችል በልዩነቶች ዙሪያ በሰከነ መንገድ የመነጋገር ባህል ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ውጤቶች፣ ከሂደቱ ባሻገር እንዲዳብሩ ከተደረጉ በሰፊውና ረዥሙ የለውጥ ሂደት ውስጥ አስፈላጊ ጉዳዮች ናቸው።

እዚህ ላይ ሁለቱም ዓይነት ውጤቶች አስፈላጊና ተመጋጋቢ መሆናቸውን መገንዘቡ ጠቃሚ ነው፡፡ የማይዳሰሱ ውጤቶች ፖለቲካዊ ሽግግርን ከማሳለጥ፣ ቀውሶችን ከመቅረፍ፣ ልዩነቶችን ከማጥበብ በተጨማሪ ለመሠረታዊ ማኅበራዊ ለውጥ መሠረት የመጣል አቅም አላቸው፡፡ ከዚህም በላይ የማይዳሰሱ ውጤቶች ተጨባጭ ውጤቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው፡፡

በምክክር ሂደቱ የተገኙ ውጤቶች የአተገባበር ምዕራፍ ጥንቃቄ የተሞላበት ዕቅድ እና ዲዛይን ያስፈልገዋል፡፡ እንደ ሀገራዊ ምክክሩ ዓላማ እና ተልዕኮ፣ የትግበራ ዕቅዱ መዘጋጀት ያለበት ምክክሩ ሲጠናቀቅ ሳይሆን በሂደት ላይ ቢሆን የበለጠ ውጤታማ እንደሆነ ይታመናል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከምክክሮቹ የሚያጠቃልላቸውን ምክረ ሀሳቦች በመቀመር አፈጻጸሙን የተመለከተ ዝርዝር ዕቅድ ለሚመለከተው አስፈጻሚ አካል የማቅረብ እንጂ የማስፈጸም ተልዕኮ አልተሰጠውም፡፡ ይህም መሆኑ በአንዳንድ ወገኖች “የሚቀርቡ ምክረ ሀሳቦች የመፈጸም ዕድላቸው በአስፈጻሚው አካል በጎ ፈቃደኝነትና ጥረት ላይ የተንጠለጠሉ መሆናቸው ክፍተት ይፈጥራል” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በሀገሪቱ በርካታ እጅግ መሠረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መሰረታዊ የሆኑ ልዩነቶች እንደመኖራቸው መጠን የሚደረስባቸውን መግባባቶች ተግባራዊ ለማድረግ ከመንግስት የተሻለ ተቋማዊ ቁመናም ሆነ አቅም ያለው አካል ባለመኖሩ ቁርጠኝነት ካለው በተሻለ ሊፈጸም የሚችልበት ዕድል ሰፊ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በዚህ መካከል ኮሚሽኑ በምክክር ሂደቱ የተደረሰባቸውን ድምዳሜዎችና ምክረ ሀሳቦች ለህዝብ በይፋ የማሳወቅ ስልጣን ያለው መሆኑ ትልቅ ጉልበት እንደሚሆነው ይታመናል፡፡ ይህ መሆኑ ህዝቡና ባለድርሻ አካላት በአስፈጻሚው አካል ላይ ተገቢውን ግፊት በማድረግ ምክረ ሀሳቦቹ ተፈጻሚ እንዲሆኑ የማድረግ እድል የሚሰጠው ከመሆኑም በላይ ለተግባራዊነታቸውም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ይታመናል፡፡

በአንጻሩም በስልጣን ላይ ያለው ገዢው ፓርቲም ሆነ በተቃዋሚዎች ዘንድ በሀገሪቱ እጅግ መሰረታዊ በሆኑ በርካታ ጉዳዮች ላይ ልዩነቶች መኖራቸው ሀገረ መንግስቱን ለማጽናት፣ ሰላምን ለማስፈን፣ ልማትና ዴሞክራሲን ለማፋጠን ለሚደረገው ጥረት አለመፋጠን ተግዳሮት መሆኑን የሚረዱ በመሆናቸውና እነዚህኑ ተግዳሮቶች ማስወገድ በህዝቡ ዘንድ ቅቡልነትን ለማግኘት ወሳኝ ጉዳይ እንደሚሆን ይገነዘቡታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም ፖለቲካዊ አንደምታው ከፍ ያለና ገሸሽ ሊደረግ የሚችል አይሆንም፡፡

በሌላም በኩል በኢትዮጵያ እጅግ መሠረታዊና ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንዲደረግ ፖለቲካዊ ፍላጎቱን ምክክር ኮሚሽኑን በአዋጅ በማቋቋም የገለጸው በስልጣን ላይ ያለው መንግስት፤ መግባባት ላይ ለሚደረስባቸው ጉዳዮች ተፈጻሚነትም ፖለቲካዊ ቁርጠኝነቱ እንዳለው በተለያዩ ወቅቶች መግለጹ እንደ ተጨማሪ አቅም የሚወሰድ ነው፡፡

የአፈፃፀሙ ምዕራፍ አስፈላጊው ገጽታ ሀገር አቀፍ ባለድርሻ አካላት የምክረ ሀሳቦቹን ዝርዝር ሁኔታ እንዲከታተሉ እና ያልተፈቱ ወይም ችግር ያለባቸው ጉዳዮች እንዲፈቱ ተገቢውን ጥረት እና በአስፈጻሚው አካል ላይ አስፈላጊውን ግፊት ማድረግ የሚያስችል ስረዓት መኖሩ ነው።