የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኦሮሚያ ክልል አጀንዳዎችን ከምክክር ባለድርሻ አካላት ወኪሎች ዛሬ ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም ተረክቧል።
የኦሮሚያ ክልል የምክክር መድረክ ከሰኞ ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም ድረስ ተካሂዷል።
በዚህ የምክክር መድረክ ከ7ሺ በላይ የህብረተሰብ ወኪሎች እና ከ1ሺ 700 በላይ የባለድርሻ አካላት ወኪሎች ተሳትፈዋል።