መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሚሽኑ አዘጋጅነት በካፒታል ሆቴል የተደረገው ውይይት ከ7 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ላይ የሚሰሩ ማህበራትን እና ድርጅቶችን ተሳታፊ አድርጓል፡፡
የውይይት መድረኩ ሁለት ዓላማዎችን አንግቦ የተነሳ ሲሆን የመጀመሪያው ወጣቶች በማህበራቱ እና በድርጅቶቹ በኩል ስለ ሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ግንዛቤን እንዲጨብጡ ማድረግ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ወጣቶች በምክክር ሂደቱ ላይ የጎላ ሚና እንዲኖራቸው ሀሳቦችን በማመንጨት ወደ ስራ ለመግባት ነው፡፡
በቀጣይም ኮሚሽኑ ወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ላይ የጎላ ሚና እንዲኖራቸው ከማህበራቱ እና ሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ እንደሚሰራ ኮሚሽኑን በመወከል በዝግጅቱ ላይ የተገኙት ኮሚሽነሮች አስታውቀዋል፡፡