በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው በዚሁ መድረክ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደቶች ላይ ንቁ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ግንዛቤን ለመፍጠር ታስቦ በተዘጋጀው መድረክ ከ 250 በላይ የተቋማት ተወካዮች ታድመውበታል፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ኮሚሽኑንና የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን በተመለከተ የተለያዩ ገለፃዎችና ማብራሪያዎች ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መሰረት ስለ ሀገራዊ ምክክር መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ፣ ሀገራዊ ምክክር ለሀገራችን ኢትዮጵያ ስላለው ፋይዳ፣ በኮሚሽኑ ስለተከናወኑ አንኳር ተግባራት እና ኮሚሽኑ ስለሚገዛባቸው የህግ ማዕቀፎች መግለጫዎችን ቀርበዋል፡፡
ገለፃውን ተከትሎ ገንቢ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን ኮሚሽኑ በመላው ሀገራችን ከሚገኙ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር ሊሰራ ስለሚችልባቸው መንገዶች የተለያዩ ምክረ-ሀሳቦች ተንሸራሽረዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ተቋማቱ በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚወክሏቸውን አካላት በመምረጥ ለሂደቱ እንዲዘጋጁ ኮሚሽነሮች ጥሪ አቅርበዋል፡፡