ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም በቦንጋ ከተማ የተጀመረው የተሳታፊዎች ልየታ መርሃ ግብር በቴፒ፣ ማሻ፣ ሚዛን፣ አማን፣ አመያ እና ተርጫ ከተሞች ቀጥሎ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ ከ 47 ወረዳዎች ከእያንዳንዳቸው 9 የማህበረሰብ ክፍሎች ሀምሳ ሀምሳ ሰዎችን መርጠው በሂደቱም በቁጥር ከ21,000 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ተካፋይ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡
ኮሚሽኑ በክልሉ ባካሄደው የልየታ መርሀ ግብር ተሳታፊዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮቻቸውን የመረጡ ሲሆን በሀገራዊ ምክክሩ ላይ እንዲንፀባረቅላቸው የሚፈልጓቸውን አጀንዳዎች በቡድን ውይይቶቻቸው አመላክተዋል፡፡