የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ በማስመረጥ ላይ ይገኛል፡፡

sheger city

በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ 1,300 የሚሆኑ የሁሉም ክፍለ ከተሞች ተሳታፊዎችን እያሳተፈ ይገኛል፡፡

በሂደቱም ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

በመቀጠልም ውይይቶች ይደረጉና ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ተወካዮች እንዲመርጡ ይደረጋል፡፡