የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በአሜሪካ ምዕራባዊ ክፍል ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ጥር 25 ቀን 2016 ዓ. ም የበይነ-መረብ ስብሰባ አደረገ፡፡

ኮሚሽኑ በአሜሪካ ምዕራባዊ ክፍል ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ጥር 25 ቀን 2016 ዓ. ም የበይነ መረብ ስብሰባ አደረገ፡ 01
ኮሚሽኑ በአሜሪካ ምዕራባዊ ክፍል ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ጥር 25 ቀን 2016 ዓ. ም የበይነ-መረብ ስብሰባ አደረገ፡፡ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2፡00 ላይ ተጀምሮ ከሦስት ሰዓታት በላይ የቆየው ይህ ስብሰባ ለውይይት ጋባዥ የሆኑ የተለያዩ ገላፃዎች እና ማብራሪያዎች ቀርበውበታል፡፡ በመድረኩ ላይ ኮሚሽኑ ራሱን በማስተዋወቅ ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ ምክክር ሂደት ሊኖራቸው ስለሚገባ ተሳትፎ እና ሊያበርክቱት ስለሚችሉ አስተዋጽዎች ሀሳቦችን አቅርቧል፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙ የኮሚሽኑ አባላት ኮሚሽኑንና የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን በተመለከተ የተለያዩ ገለፃዎችና ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡ ያንን ተከትሎ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን ኮሚሽኑ በተጠቀሰው አካባቢ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በትብብር ስለሚሰራባቸው መንገዶች ውይይት ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም የኮሚሽኑን የአሰራር ሂደት በተመለከተ ጠቃሚ ምክረ-ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአምስት ዙሮች በውጭ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ሲያከናውን የቆየውን የበይነ-መረብ ውይይት በዕለቱ በተከናወነው መርሐ-ግብር አጠናቋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የተዘጋጁት እነዚህ የበይነ-መረብ ውይይቶች ኮሚሽኑ በመላው ዓለም ከሚኖሩ ወገኖቻችን ጋር ተገናኝቶ ራሱን ለማስተዋወቅ እድል የከፈቱ ሲሆን የዲያስፖራው ማህበረሰብ በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የሚኖረው ተግባራዊ ተሳትፎ ሰለሚጎለብትበት ሁኔታ ሀሳቦች እንዲንሸራሸሩ እድል ሰጥተዋል፡፡
እስከ አሁን በተካሄዱት የበይነ መረብ ስብሰባዎች ውድ ጊዜያችሁን መስዋዕት በማድረግ ብሎም ንቁ ተሳታፊ በመሆን የኮሚሽኑ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ላበረታታችሁ፤ ግልጽ እና አስተማሪ የሆነ ትችት ላቀረባችሁ ወገኖቻችን በሙሉ ኮሚሽኑ ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

ኮሚሽኑ በአሜሪካ ምዕራባዊ ክፍል ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ጥር 25 ቀን 2016 ዓ. ም የበይነ መረብ ስብሰባ አደረገ፡ 02

 

ኮሚሽኑ በአሜሪካ ምዕራባዊ ክፍል ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ጥር 25 ቀን 2016 ዓ. ም የበይነ መረብ ስብሰባ አደረገ፡ 03

 

ኮሚሽኑ በአሜሪካ ምዕራባዊ ክፍል ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ጥር 25 ቀን 2016 ዓ. ም የበይነ መረብ ስብሰባ አደረገ፡ 04