ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ሲሰጥ የነበረውን የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና ህዳር 06 ቀን 2016 ዓ.ም አጠናቋል፡፡ በጅግጅጋ ከተማ ለሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ከስድስት ዞኖች የተውጣጡ ተባባሪ አካላት ተሳታፊዎች ሆነውበታል፡፡
በስልጠናው ላይ ተባባሪ አካላቱ ባደረጓቸው የቡድን ውይይቶች ላይ የክልሉን ዓውድ መሰረት አድርገው ከየማህበረሰብ ክፍሉ ተሳታፊዎችን ስለሚለዩባቸው መንገዶች ውይይቶች አድርገዋል፡፡ በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ተባባሪ አካላት በዞናቸው በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በመሄድ በኮሚሽኑ ከተለዩት የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎችን በመለየት ረገድ ሂደቱ ተዓማኒ እንዲሆን አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡