የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በጎዴ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የተባባሪ አካላት ስልጠና አጠኗቋል

endc gode trining

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ጎዴ ማዕከል ለተባባሪ አካላት ሲሰጥ የነበረውን ሀለተኛውን ዙር ስልጠና ዛሬ ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም አጠናቀቀ፡፡ በጎዴ ከተማ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ከአምስት ዞኖች የተውጣጡ ተባባሪ አካላት ተሳታፊዎች ሆነውበታል፡፡

በስልጠናው ላይ ተባባሪ አካላቱ ባደረጓቸው የቡድን ውይይቶች ላይ የክልሉን ዓውድ መሰረት አድርገው ከየማህበረሰብ ክፍሉ ተሳታፊዎችን ስለሚለዩባቸው መንገዶች ውይይቶች አድርገዋል፡፡ በሌላ በኩልም በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ተባባሪ አካላት በዞናቸው በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በመሄድ በኮሚሽኑ ከተለዩት የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎችን በመለየት ረገድ ሂደቱ ተዓማኒ እንዲሆን አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡