የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል ሊበን ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ዛሬ ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ፡፡

somali liben

በፊልቱ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው መርሐ-ግብር ከደቃ ሱፍቱ፣ ቀርሳ ዱላ እና ፊልቱ ወረዳዎች የተውጣጡ ተሰብሳቢዎችን እያሳተፈ ይገኛል፡፡

በሂደቱ ኮሚሽኑ ለተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች በባለሙያ ገላፃ ያደረገ ሲሆን ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ተወካዮች በመምረጥ ላይ ይገኛሉ፡፡

የሊበን ዞን የተወካዮች መረጣ ቅዳሜ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡