የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን እያደራጁ ነው

kkk min
#ኦሮሚያ ክልል
ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም
ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን  እያደራጁ ነው
በኦሮሚያ ክልል የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ከትላንት ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም ጀምረው አጀንዳዎቻቸውን በቡድን ውይይት እያደራጁ ይገኛሉ።
ባለድርሻ አካላቱ ያደራጁትን አጀንዳ ለኮሚሽኑ የሚያቀርቡ 25 ተወካዮችን መርጠው በአደራ ያስረክባሉ።
እነዚህ የሚመረጡ 25 ወኪሎች በነገው ዕለት የክልሉን አጀንዳ በዋና መድረክ አቅርበው በማፀደቅ ለኮሚሽኑ የሚያስረክቡ ይሆናል።
በኦሮሚያ ክልል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ከ1ሺ 700 በላይ ወኪሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በባለድርሻ አካላት ምክክር እየተሳተፉ የሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት፣ የህብረተሰብ ወኪሎች፣ የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንዲሁም የልዩ ልዩ ተቋማትና ማህበራት ወኪሎች ናቸው።
የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ነገ ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ይሆናል።