የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ጃፓን ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ የምታደረገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር አረጋገጡ፡፡

endc japan

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በውይይቱም በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት አሁናዊ ተግባራት በተመለከተ በዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለጻ እና ማብራርያ ተደርጎላቸዋል፡፡

አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ገላፃ እና ማብራሪያ ምስጋና አቅርበው በኢትዮጵያ እየተተገበረ የሚገኘው የምክክር ሂደት ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ባለሙሉ ተስፋ እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ ሀገራቸው ጃፓንም ለሂደቱ መሳካት የምታደረገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አምባሳደሩ አረጋግጠዋል፡፡

endc japan
endc japan