የኮሚሽኑ የስራ ዘመን ለአንድ ዓመት ተራዘመ
የካቲት 11/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ ዘመን ለአንድ አመት ተራዝሟል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባው ነው የኮሚሽኑ የስራ ዘመን እንዲራዘም ውሳኔ ያሳለፈው።
ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሶስት ዓመታት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕሮፌሰር) ቀርቦለት ከመረመረ በኋላ ነው።
ሪፓርቱን ያዳመጡት የምክርቤቱ አባላት የኮሚሽኑን የስራ አፈፃፀም አድንቀዋል።
ኮሚሽኑ የቀሩትን ስራዎች ማጠናቀቅ ይችል ዘንድም የስራ ዘመኑ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
የምክር ቤቱ አባላት ኮሚሽኑ በተሰጠው ተጨማሪ የስራ ዘመን ቀሪ ስራዎችን እንዲያጠናቅቅ አሳስበዋል።