የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

diplomat photo,,,

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከ60 በላይ ከሚሆኑ የዓለም አቀፍ ተቋማት እና ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በስካይ ላይት ሆቴል ውይይት አድርጓል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ የትብብር እና አጋርነት መድረክ ላይ ኮሚሽኑን ወክለው በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት ኮሚሽነሮች በኮሚሽኑ ስለተከናወኑ ተግባራት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ይህ ሁነት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኮሚሽኑ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በመረዳት ለበለጠ ትብብር እና አጋርነት እንዲዘጋጁ በር የሚከፍት እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የታደሙ የየተቋማቱ ተወካዮች በዝግጅቱ ላይ የቀረቡትን መረጃዎች ኮሚሽኑ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት የበለጠ ግንዛቤን ለማግኘት የረዳቸው መሆኑንና ከኮሚሽኑ ጋር በአጋርነት ለመስራት ያላቸውን ተነሳሽነት ከፍ እንዳደረገው ገልፀዋል፡፡