የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ተፈራረሙ

367469692 619872980270745 6285249553532174069 n

በሀገራችን እያታዩ ያሉ ፖለቲካዊ ችግሮች በዘላቂነት መፍትሄ ይሰጣል ተብሎ በሚጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ላይ የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተካታችነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ተፈራረሙ፡፡

የፊርማ ስነ-ስርአቱ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና የአካል ጉዳተኛ ማህበር ተወካዮች የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እና የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር ፊርማውን ተፈራርመዋል፡፡

በመግባቢያ ሰነዱ በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ላይ አካል ጉዳተኞች ከወረዳ እስከ ክልል የሚኖራቸው ውክልና፣ የውይይት መድረኮች ተደራሽነት፣ እና ሎሎች መሰል ጉዳዮች ተካተውበታል፡፡

367989806 619873060270737 815817826847662105 n