የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዚህ ሳምንት ያከናወናቸውን ዐበይት ተግባራት

tibebu t

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ የሚሳተፉ ተወካዮች የውክልና ሂደት በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡

በ12 ዞኖች ከሚገኙ 97 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች 9,300 የሚሆኑ ዜጎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በቀጣይ በሚካሄዱ የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ ከ1500 የማያንሱ ተወካዮች በክልል ደረጃ በሚካሄዱ የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ የክልሉን ነዋሪ ወክለው ይሳተፋሉ፡፡

———————-

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ የተመራ የኮሚሽኑ ልዑክ ከአማራ ክልል አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡

ኮሚሽኑ በሌሎች ክልሎች ያከናወናቸውን ስራዎች በአማራ ክልልም ማስቀጠል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በአማራ ክልል በኩል የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች ኃላፊዎች በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡

———————-

ባለፈው ቅዳሜ በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ መድረክ ለአጀንዳ አሰባሰብ የሚረዱ ግብአቶች ተገኝተዋል፡፡

የአጀንዳ ማሰባሰቢያና ለምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ተወካዮችን የመምረጫ ስርአት ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ የተዘጋጀው ሀገር አቀፍ መድረክ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል፡፡

በመድረኩ 250 የሚሆኑ ከሀይማኖት ተቋማት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ደርጅቶች፣ ከመንግስት፣ ከተለያዩ ማህበራት፣ ከሚዲያና ኪነጥበብ እንዲሁም ሌሎችም ተሳትፈዋል፡፡

———————-

ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

የተወካዮች ልየታ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ተደራሽነትን ለማስፋት የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

ከባቢያዊና ሀገር አቀፍ ሚዲያዎችን በመጠቀም መረጃዎች ተደራሽ እንዲሆኑ የተደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው፡፡

ሚዲያዎች በዜና መልክ መረጃዎችን ከመስጠት በተጨማሪ ግንዛቤ የሚስጨብጡና የተለዩ ሀሳቦች የተንሸራሸረባቸው ሰፋፊ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ጥረት አድርገዋል፡፡

ለዚህም ኮሚሽኑ ምስጋናውን እያቀረበ በቀጣይም ተከታታይነት ያላቸው ስራዎች እንዲሰሩ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

በኮሚሽኑም በኩል ከሚዲያ ዘርፉ ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተገልጧል፡፡

———————-

የኮሚሽኑ የሚ

tibebu t
tibebu t

ዲያ፣ኮሙኒኬሽንና ተደራሽነት ዘርፍ