የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሙያ ማህበራት ጋር ውይይት አካሄደ

untitled design 20251204 142516 0000

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሙያ ማህበራት ጋር ውይይት አካሄደ

ህዳር 25/2018 ዓ.ም

ኮሚሽኑ ”የኢትዮጵያ የሙያ ማህበራት የላቀ ተሳትፎ ለሀገራዊ ምክክር ውጤታማነት“በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሙያ ማህበራት ጋር የምክክር መድረክ ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አካሂዷል።

በምክክር መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) ለሀገራዊ ምክክር ውጤታማነት የሙያ ማህበራት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

እስካሁን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ እንዲሳካ ላደረጉትና አሁንም እያደረጉት ላለው አስተዋጽኦ ዋና ኮሚሽነሩ የሙያ ማህበራቱን አመስግነው በቀጣይም ኮሚሽኑ በሚተገብራቸው ስራዎች አስተዋጾ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኮሚሽኑ ትግራይ ክልልን ጨምሮ በእስካሁኑ የምክክር ሂደት ያልተሳተፉ አካላትን ለማሳተፍ ጥረት እያደረገ ስለመሆኑም በመድረኩ ተነስቷል፡፡

ከትግራይ ክልል ጋር የተለያዩ ግንኙነቶች እየተደረጉ መሆኑን እና ኮሚሽኑ የምክክሩን አስፈላጊነት ለክልሉ እያስረዳ መሆኑም ተነስቷል፡፡

የሙያ ማህበራቱም ኮሚሽኑ የሚያደርገው ጥረት ይሳካ ዘንድ እገዛ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል፡፡

በመድረኩም ላይ ኮሚሽኑ ባለፉት ሶስት አመታት ያከናወናቸው ዋና ዋና ክንውኖችና ቀሪ ስራዎቹ እንዲሁም እስካሁን ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች እና ችግሮቹን ለመፍታት ያደረገውን ጥረት በመድረኩ ላይ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡