የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚገኙ ተባባሪ አካላቱ ስልጠናን ሰጠ፡፡

357017049 261080386613398 2362755868503674080 n

በተሳታፊዎች ልየታ ሂደት እና አተገባባር ላይ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ያለመው ይህ ስልጠና ተባባሪ አካላቱ በየወረዳቸው የሚገኙ ተሳታፊዎችን በመለየቱ ሂደት ውስጥ ለኮሚሽኑ እገዛ ስለሚያደርጉበት መንገድ ግንዛቤን አስጨብጧል፡፡ ስልጠናው ሰኔ 24 እና 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ የተሰጠ ሲሆን በክልሉ ከሚገኙ 22 ወረዳዎችና 5 የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 200 ተባባሪ አካላት ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡

ከስልጠናው በተጨማሪም ሰልጣኝ ተባባሪ አካላቱ በተሳታፊዎች ልየታ ሂደትና አተገባበር ዙሪያ በግብዓትነት የሚወሰዱ አስተያየቶችን ለኮሚሽኑ አባላት አቅርበው ገንቢ ውይይት ተደርጓል፡፡ በሌላ በኩልም ተባባሪ አካላቱ ባደረጓቸው የቡድን ውይይቶች የክልሉን ዓውድ መሰረት በማድረግ ከየማህበረሰብ ክፍሉ ተሳታፊዎችን ስለሚለዩባቸው መንገዶች መክረዋል፡፡

በመጨረሻም በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ተባባሪ አካላት በክልሉ ወደሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በመሄድ በኮሚሽኑ ከተለዩት ዘጠኝ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎችን በመለየት ሂደቱ ተዓማኒ እንዲሆን አስተዋፅኦ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

357010505 261080456613391 5900833896432246916 n

357031160 261080469946723 8287509758896794597 n