የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶስት ክልሎችና በአንድ የከተማ መስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ተባባሪ አካላት ስልጠናን ሰጥቷል፡

conclusion 5

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶስት ክልሎችና በአንድ የከተማ መስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ተባባሪ አካላት ስልጠናን ሰጥቷል፡፡ በተሳታፊ ልየታ አተገባበር ላይ የተሰጠው ይህ ስልጠና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ፣ በሲዳማ እና በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር ለሚገኙ ከየወረዳው ለተውጣጡ የኮሚሽኑ ተባባሪ አካላት ነው፡፡

ስልጠናው በቦንጋ፣ሐዋሳ እና ድሬዳዋ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን የሁለት ቀናት ጊዜን ወስዶ ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ የስልጠናው ዓላማም ተባባሪ አካላቱ በየወረዳቸው የሚገኙ ተሳታፊዎችን በመለየት ሂደት ውስጥ ለኮሚሽኑ እገዛን ስለሚያደርጉበት መንገድ ግንዛቤን መፍጠር ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ስልጠናውን የሰጡት የኮሚሽኑ አባላት ከተባባሪ አካላቱ ጋር በተሳታፊ ልየታ ሂደትና አተገባበር እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና በግብዓትነት ሊወሰዱ የሚችሉ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ሰልጣኞች ተሳታፊዎችን በማስወከል ሂደት ስለሚኖራችው ገለልተኛ ተሳትፎ በየወረዳቸው በቡድን ሆነው ተወያይተዋል፡፡ በተጨማሪም ኮሚሽኑ በስልጠናው ላይ በተባባሪ አካላቱ ትብብር በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን መለየት በሚያስችለው አካሄድ ላይ መክሯል፡፡

በመቀጠልም በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ተባባሪ አካላት በየወረዳዎቹ በመሄድ በኮሚሽኑ ከተለዩት ዘጠኝ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎችን በመለየት ረገድ የሂደቱን ተዓማኒነት በተመለከተ እገዛ ያደርጋሉ፡፡

conclusion 2

conclusion 3

conclusion 4

conclusion 6

conclusion 7

conclusion 8

በተሳታፊዎች ልየታ ሂደት ላይ የሴቶች ተሳትፎ ምን ይመስላል
በተሳታፊዎች ልየታ ሂደት ላይ የሴቶች ተሳትፎ ምን ይመስላል