- የተሳታፊዎች ልየታን በተመለከተ
- ኮሚሽኑ በመላው ኢትዮጵያ ከ1ሺ 300 በላይ ወረዳዎችና በክልል የሚገኙ የከተማ አስተዳደሮች ተሳታፊዎችን ለመለየት አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡
- እስካሁን ባለው አፈጻጸም ከ850 በላይ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በአጀንዳ ግብአት ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡
- እስካሁን በነበረው ተሳታፊዎችን የመለየት ሂደት ከ130ሺ በላይ ዜጎች ተሳትፈዋል፡፡
- እነዚህ 130ሺ የህብረተሰብ ክፍሎች በአጠቃላይ 14ሺ በላይ የሚሆኑ ተወካዮቻቸውን መርጠዋል፡፡
- በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሀረር፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በማእከላዊ ኢትዮጵያ እና በጋምቤላ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የተሳታፊዎች ልየታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡
- በአሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አብዛኛው ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን በቀሪ ወረዳዎች የማጠቃለያ ስራዎች በአጠረ ጊዜ ለማከናወን እየተሰራ ነው፡፡
- በአማራና በትግራይ ክልሎች እስካሁን የተሳታፊዎች ልየታ አልተጀመረም፡፡ ሆኖም በሁለቱም ክልሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ናቸው፡፡
- የተሳታፊዎች ምርጫ በማንም ጫና እና በዘፈቀደ የሚከናወን ሳይሆን ኮሚሽኑ በዘረጋው የአሰራር ስርዓት ወይም ሰነ-ዘዴ አማካኝነት በጥንቃቄና ትኩረት ተሰጥቶት እየተካሄደ ነው፡፡
- የአጀንዳ ግብዓት የማሰባሰብ ስራን በተመለከተ
- ኮሚሽኑ የተሳታፊዎች ልየታ ባጠናቀቀባቸው አካባቢዎች ቢበዛ ከሁለት ሳምንት ባለበለጠ ጊዜ ውስጥ የአጀንዳ ግብአቶችን የማሰበሰቢያ ህዝባዊ መድረኮችን ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው፡፡
- የአጀንዳ ግብአት ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ እንዲሳተፉ የተመረጡ ወኪሎች ከወከላቸው ማህበረሰብ የአጀንዳ ሀሳቦችን የማሰባሰብ እንዲሁም በክልልና በከተማ አስተዳደር ደረጃ የተወከሉ ተወካዮችም ከወከሏቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመወያየት የአጀንዳ ሀሳቦችን የማሰባሰብ ስራ እንዲያከናውኑ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ተወካዮቹ ከወካዮቻው ጋር ተቀራርበው እንዲሰሩ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡
- ከአማራ እና ትግራይ ክልሎች ጋር በተገናኘ
3.1 አማራ ክልል፡–
- በአማራ ክልል በተደረገው ቅድመ ዝግጅት ተባባሪ አካላትን ከሞላ ጎደል በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የመለየት ስራ ተከናውኗል፡፡
- ለተባባሪ አካላት ስልጠና የሚሰጡ መምህራንን በክልሉ ከሚገኙ ዩንቨርስቲዎች በመለየት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
- በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኖ የምክክሩን ሂደት ለማስቀጠል እንዲቻል ከመንግስትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ኮሚሽኑ በቅርበት እየሰራ ነው፡፡
- በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ወገኖች ወደ ምክክሩ እንዲመጡ የኮሚሽኑ በር ክፍት ነው፡፡ አመቺ ሁኔታዎች እንዲፈጠርላቸውም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት ይሰራል፡፡
3.2 ትግራይ ክልል፡-
- በትግራይ ክልል የምክክሩን ሂደት ለመጀመር ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ንግግር ተጀምሯል፡፡
- ክልሉ ኮሚሽኑንና ምክክሩን የመቀበል ችግር የለበትም፣ አስተዳደሩ በክልሉ ለምክክሩ ሂደት መጀመር አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንደሚሰራ ያሳወቀ ሲሆን ኮሚሽኑ ቅድመ ዝግጅቶችን አጠናቆ ጥሪ እየጠበቀ ነው፡፡
- በአጠቃላይ ክልሉ በመርህ ደረጃ በምክክሩ አስፈላጊነት ላይ ተቃውሞ የለውም፣ አስፈላጊነቱ ላይ መግባባት ተደርሷል፡፡
- የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተሳትፎ በተመለከተ
- የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ከሆኑት ከአብዛኞቹ ጋር በጋራ እየሰራ ነው፡፡ ከጋራ ምክር ቤቱ ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡
- 13 የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከኮሚሽኑ ጋር እየሰሩ አይደለም፡፡
- ኮሚሽኑ ከፓርቲዎች ጋር በየጊዜው በሚያደርገው ንግግር ወደ ምክክር መድረኩ የሚቀላቀሉ ፓርቲዎችን ቁጥር ማሳደግ ችሏል፡፡
- ወደፊትም ኮሚሽኑ የተለያዩ ምክንያቶችን በማንሳት አንሳተፍም ያሉ ፓርቲዎችን በቅርበት በማነጋገር በጋራ ለመስራት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ከፓርቲዎቹም አሉ በሚሏቸው ችግሮች ዙሪያ ከኮሚሽኑ ጋር በቅርበት ለመነጋገር ጥረት ማድረግ ይጠበቃል፡፡
- የዳያስፖራው ማህበረሰብን በተመለከተ
- ኮሚሽኑ ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ጋር በቅርበት እየሰራ ነው፤ ወደፊትም ይህንኑ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
- ኮሚሽኑ የዳያስፖራውን ተሳትፎ ለማካተት በርካታ ውይይቶችን በበየነመረብ አማካኝነት አካሂዷል፡፡
- የሚድያ አጋሮችን በተመለከተ
የኮሚሽኑ የሚድያ አጋሮች ኮሚሽኑንና ምክክሩን የተመለከቱ ጉዳዮችን ለህብረተሰቡ በማደረስ ለሂደቱ መሳካት ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡ ትኩረት ሰጥቶ ከመስራት አኳያም በየጊዜው እየታዩ ያሉ መሻሻሎች አሉ፡፡
ይህ ተሳትፎ በቀጣይ በሚካሄዱ የምክክሩ ሂደቶች ላይ ተጠናክሮ እንዲሚቀጥል ይጠበቃል፡፡