የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ መረጃዎች
የካቲት 7/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከግንቦት 21/2016 ዓ.ም ጀምሮ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ኮሚሽኑ እስከአሁን በአስር ክልሎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች ወስጥ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎችን አሰባስቦ ተረክቧል፡፡
የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ የተከናወነባቸው የከተማ አስተዳደሮች
1. አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
2. ድሬዳዋ አስተዳደር ናቸው
የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ የተከናወነባቸው ክልሎች
1. ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል
2. ጋምቤላ ክልል
3. ሐረሪ ክልል
4. ሲዳማ ክልል
5. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
6. አፋር ክልል
7. ሱማሌ ክልል
8. ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል
9. የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል
10. ኦሮሚያ ክልል ናቸው፡፡
በአስሩም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በምክክር መድረኩ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት
1. የህብረተሰብ ክፍሎች ወኪሎች
2. የፖለቲካ ፓርቲዎች ወኪሎች
3. የሶስቱ የመንግስት አካላት ወኪሎች (ህግ አውጪ፣ ህግ አስፈፃሚና ህግ ተርጓሚ)
4. የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎች
5. የተቋማትና ማህበራት ወኪሎች
ምክክሩን ሂደት በተለያየ መልኩ የደገፉ አካላት
👉በጎ ፈቃደኞች
👉ተባባሪ አካላት
👉ሞደሬተሮች (አወያይ የዩኒቨርስቲ መምህራን)
በአስሩ ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በተካሄደው የምክክር ምዕራፍ ስተሳተፉ አካላት ቁጥሮች ምን ይናገራሉ?
የተሳታፊ ልየታ ተሳትፎ
👉በ975 ወረዳዎች የተሳታፊ ልየታ መድረኮች ተከናውነዋል፡፡
👉በ975 ወረዳዎች በተካሄዱ የተሳታፊ ልየታ መድረኮች 105,300 (አንድ መቶ አምስት ሺ ሶስት መቶ) አስር የማህበረሰብ መሰረቶችን የወከሉ ተሳታፊዎች ተካፍለዋል፡፡
በአስር ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች በተካሄደው የክልል የምክክር መድረኮች ደግሞ
👉614 የፖለቲካ ፓርቲዎች ወኪሎች
👉2456 የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎች
👉2483 የመንግስት አካላት ተወካዮች
👉3783 የተቋማትና ማህበራት ተወካዮች
👉15,204 የህብረሰብ ወኪሎች ተሳትፈዋል፡፡
የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የምክክር ሂደቶችን
👉206 ሞደሬተሮች
👉436 በጎ ፈቃደኞች በተለያየ መልኩ ደግፈዋል፡፡
በዚህ ሂደት ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ መግባባት ሊደረግባቸው ይገባል ያሏቸውን የአጀንዳ ሃሳቦች አደራጅተው ለኮሚሽኑ አስረክበዋል፡፡
ይህ እንዳለ ሆኖ ሂደቱ ዜጎች የዴሞክራሲ ልምምዳቸውን ከፍ ያደረጉበት እንደነበርም መገንዘብ ተችሏል፡፡
ኮሚሽኑ በአማራና በትግራይ ክልሎች ተመሳሳይ መድረኮችን የሚያካሂድ ይሆናል፡፡
                                          ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!