የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

“የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ነው፡፡” ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ

addis ababa 2

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ማሰባሰብና የሀገራዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች የግብአት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በውይይት መድረኩ ከተለያዩ ማኅበራት፣ ተቋማትና የማኅበረሰብ ክፍሎች የተወከሉ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ለውይይቱ ተሳታፊዎች አስገንዝበዋል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሂደቱ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ኮሚሽኑ እስካሁኑ ያከናወናቸው ተግባራት፣ በቅርቡ በክልሎች የሚካሄደውን የአጀንዳ ማሰባሰብ እንዲሁም ምክክርና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የማስወከል ሂደት የአሠራር ሥርዓትን የተመለከተ ገለፃ በኮሚሽኑ አባላት ለተሳታፊዎች ቀርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሳታፊዎች ልየታ በተጠናቀቀባቸው ክልሎች አጀንዳ የማሰባሰብና ተግባር በቅርቡ ማከናወን የሚጀምር ይሆናል፡፡