የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የሕብረተሰብ ክፍል ወኪሎች አጀንዳዎቻቸውን በቃለ ጉባኤ እያደራጁ ነው፡፡

አዲስ 8
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ 11 የሕብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ ከ2000 በላይ ተሳታፊዎች ከግንቦት 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ኹለት ቀናት ከወከሉት የህብረተሰብ ከፍል ይዘው በመጡት አጀንዳ ላይ ሲወያዩ ቆይተዋል፡፡
የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮቹ በዚህ ውይይታቸው እጅግ በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ተወያይተዋል፡፡
በዛሬው የጠዋት መርሃ-ግብር አጀንዳዎቻቸውን በአንድ ቃለ ጉባኤ የሚያደራጁበት ኹነትም በግዮን ሆቴል እየተከናወነ ይገኛል።
በተጨማሪም በሂደቱ ላይ በመሳተፍ የሚገኙት የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለሚደርጓቸው የምክክር መድረኮች እያንዳንዳቸው 11 ተወካዮችን መምረጥ ጀምረዋል፡፡
በከተማ አስተዳደር ደረጃ የሚካሄደው ምክክር ከየሕብረተሰብ ክፍሉ ወኪሎች በተጨማሪ የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮችን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ማህበራት ተወካዮችን ፣ የሶስቱ የመንግስት አካላት ተወካዮችን እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በማካተት በነገው ዕለት የሚጀመር ይሆናል፡፡አዲስ 8