የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ የሲዳማ ክልል የተሳታፊዎች ልየታን አድርጓል

356247899 259599763428127 4189274986883382439 n

ሰኔ 01 ቀን 2015 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የተጀመረው የሲዳማ ክልል የተሳታፊዎች ልየታ በይርጋለም፣አለታ ወንዶ እና በንሳ ከተሞች ቀጥሎ ሰኔ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ በክልሉ ከሚገኙ 45 ወረዳዎች ከተውጣጡና በእያንዳንዳቸው ከሚኖሩ ዘጠኝ የማህበረሰብ ክፍሎች ሀምሳ ሀምሳ ተሳታፊዎች የሂደቱ አካል እንዲሆኑ በማድረግ (በአንድ ወረዳ 450) በአጠቃላይ ከ20,000 በላይ ተሳታፊዎች የሂደቱ ተካፋይ ሆነዋል፡፡

ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች በተከናወኑ የልየታ መርሃ ግብሮች ላይ ተሳታፊ የነበሩ ተሰብሳቢዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮቻቸውን ከየማህበረሰብ ክፍሎቻቸው ከመምረጣቸውም ባሻገር በሀገራዊ ምክክሩ ላይ እንዲንፀባረቅላቸው የሚፈልጓቸውን አጀንዳዎች በቡድን ውይይቶቻቸው ላይ አመላክተዋል፡፡