የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በጅማ እና አዳማ ከተሞች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል

323452724 2315268528655706 8912462945688164677 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ በጅማ እና አዳማ ከተሞች ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ባለው ውይይት ላይ የተለያዩ ጉዳዮች አንስቶ ገለፃዎችን አድርጓል፡፡ የኮሚሽኑ አባላት የሀገራዊ ምክክርን ፅንሰ ሀሳብ በውይይቱ ላይ ያብራሩ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም ሀገራዊ ምክክሮችን ለማድረግ የተከናወኑ የዝግጅት ስራዎችን አቅርበዋል፡፡ ከቀረቡት የዝግጅት ስራዎች ውስጥ ተሳታፊዎችን ለመለየት የተደረጉ ዝግጅቶች ዋናውን ቦታ የሚይዙ ሲሆን በቀጣይ ሊሰሩ በታቀዱ ስራዎች ላይ ውይይትና ማብራርያ ተደርጓል፡፡ በሌላ በኩልም ከውይይቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን ለተነሱትም ጥያቄዎች የኮሚሽኑ አባላት መልሶችንና ማብራርያዎችን ሰጥቷል፡፡

በአዳማ እና በጅማ ከተሞች የተደረገ የትውውቅ መድረክ

323938713 3363490850636136 1930228026153042570 n

 

323692182 1287151908526633 4196564806192389669 n

 

323550723 627250295826661 3353782711109333609 n