የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡርጂ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ እያስመረጠ ይገኛል፡፡

burji zone

በሶያማ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ከአንድ ወረዳ እና አንድ የከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 200 የሚሆኑ ተሳታፊዎችን በማሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡

በሂደቱ ኮሚሽኑ ለተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች በባለሙያ ገላፃ የተደረገላቸው ሲሆን ከዚህ በመቀጠልም ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ተወካዮች እንዲመርጡ ይደረጋል፡፡