የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ እና ጎፋ ዞኖች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ አስመረጠ፡፡

south et gamo

በአርባ ምንጭ እና ሳውላ ከተሞች በትይዩ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የጋሞ እና ጎፋ ዞኖች የተወካዮች መረጣ ከየወረዳው የተወከሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮችን በማካተት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የጋሞ ዞን የተወካዮች መረጣ ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን 1,800 የሚሆኑ ተሳታፊዎች 20 ወረዳዎችንና የከተማ አስተዳደሮችን በመወከል ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ መርሐ-ግብሩም የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይ በሳውላ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የተወካዮች መረጣ በጎፋ ዞን የሚገኙ 11 ወረዳዎችንና የከተማ አስተዳደሮችን በማሳተፍ ለሶስት ቀናት ቆይቶ የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲጠናቀቅ እቅድ ተይዟል፡፡ በሂደቱም ወረዳዎcu በመወከል ከ1,000 በላይ ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ለመምረጥ እንደሚሰበሰቡ ይጠበቃል፡፡

በዚህ መሰረት ተሳታፊዎች ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ሁለት ግለሰቦች ከአንድ ተጠባባቂ ጋር በየወረዳቸው እና በየማህበረሰብ ይመርታሉ፡፡

 

south et gofa