የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን የተለያዩ የህበብረተሰብ ክፍሎችን በመወከል የአጀንዳ ሀሳብ የሚሰጡ ተወካዮችን መረጣ አከናወነ፡፡

west arsi

ተወካዮችን የማስመረጡ ሂደት በክልሉ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት የምዕራብ አርሲን 14 ወረዳዎች ያሳተፈ መርሐ-ግብር ተካሂዷል፡፡

በሂደቱ ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

በመቀጠልም ውይይት ተደርጎ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ተወካዮች እንዲመርጡ ይደረጋል፡፡

የዞኑ የተወካዮች መረጣ መድረክ ከ1,000 በላይ የሚሆኑ ተሰብሳቢዎችን በማሳተፍ በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡