የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ምክንያቶች በተባባሪ አካላት ስልጠና ላይ ሳይካተቱ ለቆዩ  ወረዳዎችን ተባባሪ አካላት  ስልጠና ሰጠ፡፡

oromia participants

በ8 ዞኖች ውስጥ ከሚገኙ 55 ወረዳዎች የተወከሉ 185 የሚሆኑ ተባባሪ አካላት የተሳተፉበት ይህ ስልጠና ለሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ ሲሰጥ ቆይቶ  የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡

ስልጠናውን የወሰዱ ተባባሪ አካላት ከኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣ ከአባገዳዎች፣ ከሀደ ሲንቄዎች ከማህበረሰብ መሪዎች፣ ከክልሉ ሲቪክ ማህበራት ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣  መምህራን ማህበር፣  የዕድሮች ማህበራት ጥምረት፣ ከወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ተወካይ እና የፍርድ ቤት ዳኞች ናቸው፡፡

በስልጠናው ተባባሪ አካላቱ ስለምክክር ጽንሰ ሃሳብ፤ ስለ ኮሚሽኑ ዓላማዎችና የእስካሁኑ የስራ ሂደት፣ እንዲሁም ተሳታፊዎች ስለሚለዩበት የአሰራር ስነ ዘዴ ግንዛቤ ጨብጠዋል፡፡ በቀጣይ ተባባሪ አካላቱ በየወረዳቸው ተሳታፊዎችን በገለልተኝነት  የመለየት ስራ ይሰራሉ ፡፡