የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙት አባገዳዎች እና ሀደሲንቄዎች ጋር ተወያይቷል

oromia

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ  ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም በአዳማ ከተማ አዘጋጀ፡፡ በመድረኩ ላይ አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች የተገኙ ሲሆን በክልሉ በሚከናወኑ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ ሚና እና ተሳትፎ በሰፊው ተብራርቶ ውይይት በመደረግ ላይ ነው፡፡

በዝግጅቱ ላይ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነርን ጨምሮ ሌሎች የኮሚሽኑ አባላት ተገኝተዋል፡፡

ዝግጅቱን የታደሙት አባ ገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች ችግሮችን በምክክር እና በውይይት መፍታት ትርፋማ እንደሚያደርግ ጠቁመው የኮሚሽኑን ስራዎች ለመደገፍ ያላቸውን ተነሳሽነት ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩልም እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት ኮሚሽኑ የክልሉን ዓውድ ያገናዘበ አሰራር ተከትሎ እንዲሰራ ከታዳሚዎች ምክረ ሀሳቦች እየቀረቡ ያሉ ሲሆን ገንቢ ውይይቶችም በማደረግ ላይ ይገኛሉ፡፡