የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ፡፡

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ 01
ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ፡፡ ዛሬ ጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም በጅግጅጋ እና ጎዴ ከተሞች በትይዩ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የፋፈን ዞን እና የሸበሌ ዞን የተወካዮች መረጣ ከየወረዳው የተወከሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮችን በማካተት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በጅግጅጋ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የፋፈን ዞን የተወካዮች መረጣ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ1600 በላይ ተሳታፊዎች 14 ወረዳዎችን በመወከል ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ በዛሬው ዕለት እየተከናወነ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ ከጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር፣ አውበሬ ወረዳ፣ ሙላ ወረዳ እና ቱሉጉሌድ ወረዳ የተውጣጡ ተሳታፊዎች የሂደቱ አካል በመሆን ላይ ናቸው፡፡ በዞኑ የሚካሄደው መርሐ-ግብር የተቀሩትን ወረዳዎች በማካተት እሁድ የካቲት 03 ቀን 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ በጎዴ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የተወካዮች መረጣ በሸበሌ ዞን የሚገኙ 11 ወረዳዎችንና የከተማ አስተዳደሮችን በማሳታፍ ለሶስት ቀናት ቆይቶ ቅዳሜ የካቲት 02 ቀን 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡ በሂደቱም እነዚህን ወረዳዎች በመወከል 1100 የሚደርሱ ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን እንደሚመርጡ ይጠበቃል፡፡ ዛሬ እየተከናወነ በሚገኘው መርሐ-ግብር ከጎዴ ከተማ አስተዳደር፣ ጎዴ ወረዳ፣ ደናን ወረዳ እና ቤር አኖ ወረዳ የተውጣጡ ተሳታፊዎች የሂደቱ አካል በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡
በሁለቱም ከተሞች እየተካሄዱ የሚገኙት መርሐ-ግብሮች ለተሳታፊዎች ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ስለ ኮሚሽኑ ገላጻዎች እንዲደረጉ አስችለዋል፡፡ በዚህ ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን ሲመርጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ሂደቶች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ የቀረበውን ገለፃ እና ማብራሪያ ተከትሎም ውይይት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
በመቀጠልም ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ሁለት ግለሰቦች ከአንድ ተጠባባቂ ጋር በየወረዳቸው እና በየማህበረሰብ ክፍሎቻቸው ይመርጣሉ፡፡

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ 02

 

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ 03

 

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ 04

 

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ 05

 

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ 06

 

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ 07

 

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከየማህበረሰብ ክፍሉ ማስመረጥ ጀመረ 08