የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን እያስመረጠ ነው፡፡

west haharge

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከሚገኙ 9 ወረዳዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን የሚያስመርጥበትን መርሐ-ግብር አስጀምሯል፡፡

በሐረር ከተማ ጨለንቆ የባህል አዳራሽ በመከናወን ላይ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ከ800 በላይ የማህበረሰብ ተወካዮችን እያሳተፈ ይገኛል፡፡

በዚህ መርሐ-ግብር ከበዴሳ ከተማ አስተዳደር፣ ከዳሩ ለቡ፣ ከሜኤሶ፣ ከጭሮ፣ ከዶባ፣ ከሸነን ዲጎ፣ ከኦዳ ቡልቱ ፣ከቦኬ እና ከአንጫር ወረዳዎች የመጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች በአጀንዳ ልየታ የሚሳተፉ ተወካዮቻቸውን የሚመርጡ ይሆናል፡፡

በትላንትናው እለት በምእራብ ሐረርጌ አዊ ጉዲና፣ገመቺስ፣አብሮ፣ጉምቢ ቦርዶዴ፣ቡርቃ ዲምቱ፣ጉባ ቆርቻ እና ጡሉ ከተባሉ 7 ወረዳዎች የተውጣጡ 700 የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተው ወኪሎቻቸውን መምረጣቸው አይዘነጋም፡፡

west haharge
west haharge