የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ 8 ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ተሳታፊዎች ጋር ስብሰባን አድርጓል

356417931 259600376761399 3478735563252624723 n

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ 8 ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡና እያንዳንዳቸውም 9 የማህበረሰብ ክፍሎችን ወክለው ከመጡ 3,600 ተሳታፊዎች ጋር ሐሙስ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ስብሰባን አድርጓል፡፡ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ አዳራሽ እና በሐዋሳ ሚሊኒየም አዳራሽ የተደረገው ይህ ስብሰባ ለሚቀጥለው የምክክር ሂደት አስፈላጊ የሆኑ ተግባራት አከናውኗል፡፡

በስብሰባው ላይ ሁለት ክንውኖች የተካሄዱ ሲሆን በጠዋቱ መርሀ ግብር ላይ ስለ ኮሚሽኑ ስራዎችና ስለ አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት በኮሚሽኑ አካላት ለተሰብሳቢዎቹ ገለፃ ተደርጓል፡፡ በመቀጠልም ከየወረዳው ተወክለው የመጡ ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚወክሏቸውን ሁለት ሁለት ግለሰቦች የመረጡ ሲሆን ይህም በከሰዓቱ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡ በተጨማሪም ተሰብሳቢዎቹ በምክክር ሂደቱ ውስጥ ቢነሱ ያሉዋቸውን አጀንዳዎች በቡድን ውይይቶቻቸው ውስጥ አመላክተዋል፡፡

ኮሚሽኑ የሚያከናውነው የተሳታፊዎች ልየታ በሐዋሳ ዙሪያ ወረዳዎች እና በሲዳማ ክልል የዞን ከተሞች በቀጣዮቹ ጊዜያት እየተከናወነ ይቀጥላል፡፡

352942126 247917431263027 4942511353280282612 n

356234294 259599903428113 4435041703007664672 n

356261449 259600343428069 3659577330631956455 n

356378772 259599790094791 8859810950890356808 n