የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በአዳማ ከተማ የውይይት መድረኮችን አካሂዷል

347136482 1433881280853606 3101540898748078607 n

ታህሳስ 22-23 ቀናት 2015 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሲቪክ ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም የዞኖችና ወረዳዎች ኃላፊዎች ጋር በአዳማ ከተማ የውይይት መድረኮችን አካሂዷል፡፡

በሁለቱ ቀናት የውይይት መድረኮች ተሳታፊዎች ኮሚሽኑ ባዛጋጃቸው የአሰራር ስርዓቶች ላይ አስተያቶችን የሰጡ ሲሆን በቡድን ውይይቶችን በማካሄድ በርካታ ግብዓቶችን ሰጥተዋል፡፡