የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከዛሬ ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ 01
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን ከዛሬ ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከየማህበረሰብ ክፍሉ እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በወራቤ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ መርሐ-ግብር ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን 10 ወረዳዎችንና 5 የከተማ አስተዳደሮችን የሂደቱ አካል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በሂደቱም ከ1500 በላይ ተሳታፊዎች ወረዳዎቻቸውን እና የማህበረሰብ ክፍሎቻቸውን በመወከል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚወክሏቸውን ግለሰቦች ይመርጣሉ፡፡
ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ 500 ተሳታፊዎች በሂደቱ ላይ በማሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ በመርሐ-ግብሩ ላይ ለተሳታፊዎች ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ሰለሀገራዊ ምክክር ሂደቶች እና ተሳታፊዎች በተወካዮች መረጣ ሂደት ላይ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች በኮሚሽኑ ባለሙያ ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን ያንን ተከትሎም ውይይት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
በመቀጠልም ከዚህ ቀደም ሲደረግ እንደነበረው ተሳታፊዎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ሁለት ግለሰቦችን ከአንድ ተጠባባቂ ጋር በየወረዳቸው እና በየማህበረሰብ ክፍሎቻቸው ይመርጣሉ፡፡